#Ethiopia | በእነ ኃይሌ ገብረስላሴና በእነ ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ኦሎምፒክ ኮሚቴ መካከል የነበረው
ከአንድ ዓመት በላይ የፈጀው በእነ ኃይሌ ገብረስላሴና በእነ ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ኦሎምፒክ ኮሚቴ መካከል የነበረው የፍ/ቤት ክርክር እንዲዘጋ ተወሠነ
በእነ ኃይሌ ገብረስላሴና በእነ የተከበሩ ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት በመደበኛ ፍ/ቤት ላሉፉት ሁለት ዓመታት ሲታይ መቆየቱ ይታወሳል።
በእነዚህ ሁለት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ እነ ኃይሌ በፍ/ቤት የኦሎምፒክን ማንኛውንም እንቅስቃሴ ሲያሳግዱ የእነ ዶክተር አሸብር ኦሎምፒክ በበኩሉ ዕገዳውን ሲያስነሳ ዓመታትን ቅርጥፍ አድርጎ መብላቱ ይታወሳል።
አሁን ከደቂቃዎች በፊት ከሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል ታማኝ ምንጮች እንዳገኘነው ዜና ከሆነ ድል ወደእነ ዶክተር አሸብር እንዳዘነበለች ይጠቁማል።
እንደ እነዚሁ ታማኝ የመረጃ ምንጮቻችን ከሆነ የሁለቱን ወገኖች ክስ ሲመረምር የነበረው የኢ.ፊ.ድ.ሪ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ዛሬ በዋለው ችሎት በሁለቱ ወገንች መካከል የተከፈተው የክርክር መዝገብ እንዲዘጋና መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት እንዲመለስ ውሳኔ አሳልፏል።
እንደ እነዚሁ ታማኝ የሀትሪክ የመረጃ ምንጮች ከሆነ ጉዳዩን ከአንድ ዓመት በላይ ሲመረምር የነበረው ፍ/ቤት ስፖርታዊ ጉዳዮች መፈታት ያለባቸው በስፖርቱ ህግና ደንቦች እንጂ በመደበኛ ፍ/ቤቶች አይደለም በማለት የክርክር መዝገቡ እንዲዘጋ ውሳኔ መተላለፉና መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መዝገብ ቤት እንዲመለስ የመጨረሻ ውሳኔ መሠጠቱን እነዚሁ ምንጮቻችን ጨምረው ገልፀውልናል።
በቅርቡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ከአስተዳደር ችግር ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ችግር በደጋፊዎች ክስ ቢመሠረትም ጉዳዩ በሽምግልና ቢፈታም ጉዳዩን ወደ መደበኛ ፍ/ቤት የወሠዱት ከሳሾች ጉዳያቸውን በስፖርቱ ህግ የማይፈቱና ክሱን የማያነሱ ከሆነ ፌዴሬሽኑ ክለቡን አግዳለሁ ማለቱ የሚዘነጋ አይደለም።
✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)
Source: GetuTemesgen









No comments yet.