ያለ ፈቃድ የሚሰጡ የኤአይ ስልጠናዎች በሕግ እንደሚያስጠይቁ ተገለጸየኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በቅርቡ ባወጣ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ያለ ፈቃድ የሚሰጡ የኤአይ ስልጠናዎች በሕግ እንደሚያስጠይቁ ተገለጸ
የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በቅርቡ ባወጣው መግለጫ በአገሪቱ ውስጥ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም በኤአይ (AI) ዘርፍ ስልጠና መስጠት የሚችሉት ራሱ ኢንስቲትዩቱና ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው ተቋማት ብቻ መሆናቸውን አረጋግጧል።
የኢንስቲትዩቱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ዘውዴ ከአዲስ ኤፍኤም 97.1 ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ተቋም በዚህ የቴክኖሎጂ ዘርፍ ትምህርት ለመስጠት አስቀድሞ የብቃት ማረጋገጫ ሊኖረው እንደሚገባ አሳስበዋል።
ዳይሬክተሩ አክለውም ኢንስቲትዩቱ እስካሁን ባለው ሂደት ለማንኛውም የግል ተቋምም ሆነ ግለሰብ በዘርፉ የማሰልጠን ፈቃድ አለመስጠቱን በግልጽ አስታውቀዋል። በመሆኑም ይህንን መመሪያ ተላልፎ የሚገኝ አካል በሕግ ተጠያቂ እንደሚሆን ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።
ከሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ጀምሮ ግን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ስልጠና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና በዩኒቨርሲቲ ደረጃ በይፋ መሰጠት እንደሚጀምርም ተመልክቷል።
በአዋጅ ቁጥር 510/2014 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ማህበረሰቡን የማሰልጠንና ለዘርፉ ምቹ ሁኔታዎችን የመፍጠር ኃላፊነት የኢንስቲትዩቱ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ሕዝቡ ፈቃድ በሌላቸው አካላት በሚደረጉ አደናጋሪ ስልጠናዎች እንዳይታለልና ለአላስፈላጊ ወጪ እንዳይዳረግ ጥሪ ቀርቧል።
ማንኛውም በዘርፉ መሰማራት የሚፈልግ አካል ከኢንስቲትዩቱ ጋር በመቀናጀት የአገሪቱን የኤአይ ፖሊሲና ስትራቴጂ መሰረት አድርጎ መንቀሳቀስ እንዳለበት ተገልጿል።
Via የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት
ኃይለሚካኤል
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: