በበረሀ የሚጮኽ የፍጹም ባህታዊ ድምጽ

- Advertisement -
Sidebar AD

🙏

በሉቃስ 1÷14 እንደተጻፈው ቅዱስ ገብርኤልና አባቱ ትንቢት የተናገሩለት፤ ከሕፃንነቱ ጀምሮ እግዚአብሔርን ያገለገለ፤ በፍጹም ልቡ ዓለምን የናቀ፤ ከተድላዋና ከደስታዋም የተለየ፤ አምላክን ለማጥመቅ የታደለ ሐዋርያ፣ መምህር፣ ሰማዕት፣ ባሕታዊ፣ ነቢይ፣ ጻድቅ ነው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ተወለደ። ዮሐንስ ማለት እግዚአብሔር ጸጋ ነው ማለት ነው፡፡ ካህኑ ቅዱስ ዘካርያስና ሚስቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሁሉ በመፈጸም ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ፡፡ ኤልሳቤጥም መካን ነበረች ልጅ እንዲሰጣቸው እግዚአብሔርን ዘወትር ይማጸኑት ነበር። ካህኑ ዘካርያስ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ ዕጣን በማሳረግ ላይ ሳለም የእግዚአብሔር መልአክ በዕጣኑ መሠዊያ ቀኝ ቆሞ ጸሎቱ እንደ ተሰማ ነገረው፡፡

ሚስቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ እንደምትወልድ፣ ስሙንም ዮሐንስ እንደሚለው፤ ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ እንደሚሞላበት ነገረው፡፡ ካህኑ ዘካርያስም መልአኩን “እኔ ሽማግሌ ነኝ፤ ሚስቴም አርጅታለችና ይህን በምን አውቃለሁ?” አለው፡፡ መልአኩም “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፤ እነሆም በጊዜው የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንህ ይህ ነገር እስከሚኾን ዲዳ ትሆናለህ፤ መናገርም አትችልም” አለው፡፡ የማገልገሉም ወራት ሲፈጸም ወደ ቤቱ ሔደ፤ ከሁለት ቀን በኋላም አረጋዊቷ ቅድስት ኤልሳቤጥ ፀነሰች፡፡ ቅድስት ኤልሳቤጥም በመካንነቷ ከሰዎች የሚደርስባት ሽሙጥ ተወግዷላታልና “እግዚአብሔር በዚህ ወራት ከሰው ስድቤን ያርቅ ዘንድ እንዲህ አደረገልኝ” ስትል ለአምስት ወራት ተሸሸገች፡፡

ጌታችን ሊወለድ ስድስት ወራት ሲቀረው፣ ሰኔ 30 ቀን ንዑድ፣ ክቡር የሆነው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ተወለደ፡፡ አንደበቱ ተይዞ የነበረው ካህኑ ዘካርያም ስሙ “ዮሐንስ” ይባል ብሎ ሲጽፍ አፉ ተከፈተ፤ አንደበቱም ተፈታ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶም የቅዱስ ዮሐንስን ነቢይነትና አጥማቂነት ተናገሯል፡፡ በዚህም ምክንያት መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በበረሀ የሚጮኽ የአዋጅ ነጋሪው ቃል ተብሎ ይገለጻል፡፡የገዳማዊ ሕይወት ምሣሌ የሆነውን መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ስናስብ የገዳማውያንን ጸጋ፣ ገዳማውያንን መደገፍና፣ በዓታቸውንም ማጽናት ምን ያህል ግዙፍ የበረከት ሥራ እንደሆነ እንረዳለን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: