አሜሪካ በኤርትራ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ እንድትቀጥል ሂውማን ራይትስ ዎች ጥሪ አቀረበ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት በኤርትራ ላይ የጣለው ማዕቀብ እንዲነሳ መደረጉ ወደፊት ይበልጥ የከፉ የሰብዓዊ መብት ረገጣዎች እንዲፈጸሙ ዕድል ይሰጣል ሲል ሂውማን ራይትስ ዎች አስጠነቀቀ።

ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ በትግራይ ጦርነት ወቅትም ሆነ በኤርትራ ውስጥ ለተፈጸሙ ግፎች ተጠያቂነት ሳይረጋገጥ ማዕቀቡን ማንሳት አደገኛ መሆኑን ገልጿል።

የኤርትራ መንግሥት ካለበት አፋኝ የፖለቲካ ሥርዓት ወጥቶ ተጨባጭ የሆኑ የለውጥ እርምጃዎችን እስኪያሳይ ድረስ ዓለም አቀፉ ጫና ሊላላ አይገባም ብሏል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ካናዳና የአውሮፓ ኅብረት ከኤርትራ ጋር የሚያደርጉት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሽፋን የሚሰጥና ተጠያቂነትን የሚያዳፍን የጥቅም ልውውጥ እንዳይሆን ድርጅቱ አሳስቧል።

በተጨማሪም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በኤርትራ ጉዳይ ላይ የመደበው የልዩ ሪፖርተር የሥራ ዘመን በመጪው ሐምሌ ወር እንዲራዘም ሂውማን ራይትስ ዎች ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጥሪ አቅርቧል።

በአገሪቱ ያለው የሰብዓዊ መብት አያያዝ አሁንም እጅግ አሳሳቢ መሆኑን የጠቀሰው ተቋሙ፣ ያለ ተገቢው ክትትልና ፍትሕ የሚደረግ ማንኛውም ዓይነት የዲፕሎማሲ መቀራረብ ለተጎጂዎች የሚሰጠውን የፍትሕ ተስፋ አደጋ ላይ ይጥላል ሲል በዝርዝር አስታውቋል።

#ኤርትራ #ሰብዓዊመብት #አሜሪካ #ማዕቀብ #ሂውማንራይትስዎች #የዓለምዜና #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2