❗️የኢራኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሜሪካን “በግድየለሽነት ወታደራዊ ጀብዱ” ከሰሱ
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ “የዲፕሎማሲ መፍትሔ በጠረጴዛ ላይ ባለ ቁጥር” አሜሪካ “ግድየለሽ ወታደራዊ ጀብዱን” ትመርጣለች በማለት ከሰሱ።
ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አባስ አራግቺ ኢራን ለአሜሪካ ግፊት “በፍጹም አትንበረከክም” ያሉ ሲሆን ፤ ይህን ያሉትም ሁለቱ ወገኖች በሆርሙዝ የባህር ስርጥ ውስጥ እርስ በርስ ጥቃት ሰንዝረዋል ከተባባሉና አሜሪካ በኢራን መርከቦች ላይ ተኩስ ከከፈተች ከአንድ ቀን በኋላ በኤክስ (X) ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ነው።
ምንም እንኳን ግጭቶች ቢኖሩም፥ ፕሬዝዳንት ትራምፕ የተኩስ አቁም ስምምነቱ እንደጸና መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ ስምምነት አሜሪካ እና እስራኤል በየካቲት ወር የጀመሩትን ጦርነት ለማቆም የሚያስችሉ ንግግሮችን ለማድረግ ያለመ ነው።
እንደ አሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ገለጻ፥ ኢራን ለአሜሪካ የሰላም ጥያቄ የሰጠችው ምላሽ አርብ ዕለት ይጠበቅ ነበር። ሩቢዮ በጣሊያን ባደረጉት ጉብኝት ወቅት “ጥያቄው ቁምነገር ያለው እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል ።
@seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.