#FastMereja I በ1.9 ቢሊዮን ብር የ”ፊንቴክ” ኢንቨስትመንት ማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ ታዋቂ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች በዋስትና ከእስር እንዲፈቱ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት ወሰነ። ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ ከ400 ሺህ እስከ 500 ሺህ ብር በሚደርስ የገንዘብ ዋስትና ከእስር ተፈትተው ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ የፈቀደ ቢሆንም፣ በአምስተኛ ተከሳሽ መንሱር ጀማል ላይ ግን አቃቤ ህግ ባቀረበው መቃወሚያ ምክንያት ውሳኔ ለመስጠት ለዛሬ ከሰዓት ቀጠሮ ይዟል ሲል ሸገር ሬዲዮ ነው የዘገበው።
Source: FastMereja








No comments yet.