#FastMereja I የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬው የአምስተኛ ቀን ውሎው “ዋልድባ አብረንታት ገዳምን ይወቁ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ መጽሐፍ በየትኛውም አህጉረ ስብከት እንዳይሰራጭ አገደ። መጽሐፉ በእምነት አስተምህሮ ላይ ጉድለት ያለበትና ለክፍፍል የሚዳርግ ነው ተብሏል።
ከዋልድባ ገዳም ጋር በተያያዘ የቀረበው መጽሐፍ በቤተክርስቲያኗ የሊቃውንት ጉባኤ ተመርምሮ፤ “እመቤታችን ከሰማይ እንደወረደች አድርጎ የሚያሳይ፣ የምሥጢራተ ቤተክርስቲያንን ቁጥር የሚያፋልስና ለመነኩሴ የማይገባ ስድብና ትችት የበዛበት” መሆኑ ተገልጿል። በዚህም ምክንያት መጽሐፉ እንዲወገዝ በሊቃውንቱ የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ ምልዓተ ጉባኤው ተመልክቶታል።
ይሁን እንጂ ሲኖዶሱ መጽሐፉን ከማገድ ባለፈ፣ የሊቃውንት ጉባኤ የጽሑፉን ባለቤትነትና ጸሐፊውን ለይቶ ባለማቅረቡ ጉዳዩ በድጋሚ ተጣርቶ ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲቀርብ መርቷል። እስከዚያው ድረስ ግን የገዳሙ አባቶች በሰላምና በፍቅር እንዲቆዩና መጽሐፉም ከሥርጭት ውጪ እንዲሆን ጥብቅ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
Source: FastMereja









No comments yet.