ከመጪው ሰኔ 24/2018 ዓ/ም ጀምሮ የሚሰጠውን የተዘጋጀ የመፈተኛ ክፍል መግቢያ ካርድ (Admission Card) በፈተና አስተዳደር ሲስተም (https://exam.eaes.et/) ከ03/09/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለክልል ትምህርት ቢሮ፣ ለዞን ትምህርት መምሪያዎች እና ለትምህርት ቤት ተወካዮች መለቀቁን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
አገልግሎት መ/ቤቱ ፦
1. እያንዳንዱ ተፈታኝ ተማሪ በአድሚሽን ካርዱ ጀርባ ላይ የትምህርት ቤቱን ወይም የወረዳው አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ማህተም የተደረገበትን አድሚሽን ካርድ ከትምህርት ቤቱ ወስዶ በእጁ መያዝ መያዝ እንዳለበት አሳስቧል።
2. በምዝገባ ወቅት በተፈታኙ ወይም በመዝጋቢው የተከሰተ የትምህርት መስክ ፣ የጾታ ፣ የፎቶ እና መሰል ማስተካከያዎች ካሉ ከግንቦት 30/2018 ዓ.ም በፊት ለትምህርት ቤቱ ማሳወቅና ሂደቱን ጠብቆ መስተካከሉንም ከትምህርት ቤቱ ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልጿል።
3. እያንዳንዱ ተፈታኝ አድሚሽን ካርዱን ወደ መፈተኛ ማዕከል ሆነ መፈተኛ ክፍል ለመግባት የሚጠቀምበት በመሆኑ በአግባቡና በጥንቃቄ እንዲይዝ አሳስቧል።
4. ተፈታኞች ፈተና ላይ ከአድሚሽን ካርድ በተጨማሪ የፋይዳ መታወቂያ መያዝ እንደሚጠበቅባቸው ገልጿል።
@tikvahethiopia
Source: Yeneta Tube








No comments yet.