“የመደመር መንግሥት” መጽሐፍ የዓረብኛ ትርጉም ነገ በአቡዳቢ ይመረቃል

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “የመደመር መንግሥት” መጽሐፍ የዓረብኛ ትርጉም ነገ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም በተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ አቡዳቢ በድምቀት ይመረቃል። ይህ ትርጉም በመካከለኛው ምሥራቅ ለሚገኙ የዓረብኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሀገራትና ሕዝቦች የኢትዮጵያን የመደመር እሳቤና የለውጥ ጉዞ በጥልቀት ለማስተዋወቅ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

​በተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ መጽሐፉ ወደ ዓረብኛ የተተረጎመው ኢትዮጵያ በመካከለኛው ምሥራቅ ያላትን የጂኦ-ፖለቲካዊ እና የጂኦ-ስትራቴጂክ ጥቅሞች ለማስጠበቅ ካላት ፍላጎት አንጻር ነው። የመደመር ፍልስፍናን በቀጣናው ቋንቋ ይዞ መቅረብ፣ የአረቡ ዓለም ስለ አዲሲቷ ኢትዮጵያ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ የለውጥ ማዕቀፎች ግልጽ ግንዛቤ እንዲኖረው ትልቅ አቅም ይፈጥራል።

​በነገው የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የንጉሣዊ ቤተሰብ አባላት፣ ዲፕሎማቶች፣ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገራት ተወካዮች እና የዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት እንደሚገኙ ይጠበቃል። ይህ ዲፕሎማሲያዊ ፋይዳ ያለው ኩነት ኢትዮጵያ ከአረቡ ዓለም ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ግንኙነት ይበልጥ ያጠናክራል ተብሎ ታምኖበታል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2