#Ethiopia | የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለሁለት ቀናት ለሚቆይ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ቤጂንግ የገቡ ሲሆን፣ በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በከፍተኛ የቻይና ባለስልጣናት ደመቅ ያለ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ፕሬዝዳንቱ ከኤር ፎርስ ዋን አውሮፕላን ሲወርዱ በቻይናው ምክትል ፕሬዝዳንት ሃን ዠንግ የተመራ ከፍተኛ ልዑክ በአውሮፕላን ማረፊያ ተገኝቶ ተቀብሏቸዋል።
ቤጂንግ ትራምፕን ለመቀበል የሀገሪቱን ከፍተኛ መሪ መላኳ፣ ለፕሬዝዳንቱና ለሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የሰጠችውን ትልቅ ቦታ የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል።
ይህም እ.ኤ.አ በ2017 ትራምፕ ወደ ቻይና ባቀኑበት ወቅት ዝቅተኛ ማዕረግ ባላቸው አማካሪ ከተደረገላቸው አቀባበል ጋር ሲነፃፀር ትልቅ ለውጥ የታየበት ነው።
በአውሮፕላን ማረፊያው በተዘጋጀው የክብር ስነ-ስርዓት ላይ ወታደራዊ ባንድ ሙዚቃ ሲያቀርብ፣ በርካታ ሰዎች የሁለቱን ሀገራት ባንዲራ እያውለበለቡ ለፕሬዝዳንቱ ያላቸውን አክብሮት ገልጸዋል።
በፕሬዝዳንት ትራምፕ ልዑክ ውስጥ ታዋቂው የቴክኖሎጂ ባለሀብትና የቴስላው ባለቤት ኤሎን ማስክን ጨምሮ የበርካታ ግዙፍ ኩባንያዎች ዋና ስራ አስፈፃሚዎች መካተታቸው የጉብኝቱን የኢኮኖሚና የቴክኖሎጂ አጀንዳዎች ክብደት አመላካች ሆኗል።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ከቻይናው አቻቸው ሺ ጂንፒንግ ጋር በሁለትዮሽ፣ በንግድ እና በዓለም አቀፍ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#TrumpInChina #USChinaRelations #DonaldTrump #HanZheng #ElonMusk #BeijingVisit #GlobalNews #Diplomacy #NewsUpdate
Source: GetuTemesgen








No comments yet.