የምክር ቤቱ መመለስ “ትግራይ እንደ ህዝብ እንድትቀጥል ለማድረግ ነው” ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል

- Advertisement -
Sidebar AD

#FastMereja I የትግራይ ምክር ቤት ወደ ቀድሞ ስራው መመለሱ የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ከተፈረደበት ውሳኔ የሚታደገውና ህልውናውን የሚያረጋግጥ መሆኑን የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ገለጹ።

ፕሬዝዳንቱ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ከተጣሰ ከሦስት ዓመታት በላይ ማለፉን ጠቁመው፣ ህዝቡ ችግሮች በሰላም ይፈታሉ በሚል በትዕግስት ቢጠባበቅም ውጤት አለመገኘቱን አስታውቀዋል። የተጣሰውን ስምምነት ብቻ ይዞ መቀጠል ህዝብን አሳልፎ ከመስጠትና “በአንገት ላይ ተረግጦ ከመኖር” የማይተናነስ በመሆኑ፣ የምክር ቤቱን ህጋዊነት ወደ ነበረበት መመለስ ህዝቡን ከከፋ አደጋ ለማውጣት የተወሰነ አስፈላጊ እርምጃ መሆኑን አስረድተዋል።

ይህ ለጦርነት መነሻ ሊሆን እንደማይችል የተናገሩት ዶ/ር ደብረፅዮን፣ ዋና ዓላማው የተረጋጋና የተሟላ አስተዳደራዊ መዋቅር በመፍጠር የህዝብን ደህንነት ማስጠበቅ እንደሆነ ገልጸዋል። አሁን ያለውን ቀውስ ለመሻገርም ሁሉን አቀፍ መንግስት ለመመስረት የሚያስችሉ ስራዎች በጥንቃቄ መጀመራቸውንና ሁሉንም የህዝብ አቅሞች የማስተባበር ተግባር እየተከናወነ እንደሚገኝ ፕሬዝዳንቱ በዝርዝር አመልክተዋል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2