የአራዳ ጊዮርጊስ የሕክምና ማዕከል 20ኛ ዓመቱን አከበረ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​ለ20 ዓመታት በጤናው ዘርፍ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው የአራዳ ጊዮርጊስ የሕክምና ማዕከልና የኢፍሶል ኢንተርናሽናል አካዳሚ፣ የ20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እና አዲሱን የአንገት በላይ (ENT) ስፔሻላይዝድ ማዕከል ምረቃ በድምቀት አከበረ።

በምረቃው ወቅት እንደተገለጸው፣ ማዕከሉ ባለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት ከ400 ሺህ በላይ ዜጎችን ከማከሙ ባለፈ በስሩ በሚገኘው የጤና ኮሌጅ ከ3,500 በላይ ነርሶችና ላብራቶሪ ባለሙያዎችን አሰልጥኖ አስመርቋል።

አዲሱ የENT ማዕከል በአዲስ አበባ ካሉ ጥቂት (5 ብቻ) መሰል ተቋማት አንዱ ሲሆን፣ በዘርፉ ያለውን ከፍተኛ የአገልግሎት ክፍተት ለመሙላትና ዘመናዊ የሕክምና መሣሪያዎችን በማሟላት ለአገልግሎት ተደራሽ መሆኑ ተገልጿል።

​የማዕከሉ መሥራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ነጋ ገብረሚካኤል እንደገለጹት፣ ተቋሙ በምስረታው ወቅት የነበረበትን የባለሙያና የመሣሪያ እጥረት ተቋቁሞ ለዚህ ደረጃ መብቃቱን ገልጸው፣ ለዚህም የሲስተር የሺ እና ላለፉት 15 ዓመታት በማማከርና በማስታወቂያ ድጋፍ ከጎናቸው ያልተለዩትን ግለሰቦች አመስግነዋል።

ማዕከሉ ከሕክምና አገልግሎቱ ጎን ለጎን ከዩኤስ ኤይድ (USAID) ጋር በመተባበር በኤች አይ ቪ (HIV) ምርመራና በበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ በስፋት ሲሳተፍ መቆየቱ ተጠቅሷል።

በቀጣይም አገልግሎቱን ይበልጥ በማዘመን ወደ “ዲጂታል ጤና” ለመሸጋገር፣ የኩላሊት እጥበትና የካንሰር ሕክምናን ለመጀመር እንዲሁም አገልግሎቱን በመላው ኢትዮጵያ ለማስፋፋት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን በማብሰር፣ ለ25ኛ ዓመት የብር ኢዩቤልዩ በዓል በሰላም ለመድረስ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: