የአጥንት ጤና ለጭንቅላት ንቃትና ለትውስታ ያለውን ወሳኝ ሚና ተመራማሪዎች ይፋ አደረጉ
አጥንቶቻችን የሰውነታችንን ቅርፅ ከመያዝ ባለፈ እንደ ልብ እና ሳንባ ሁሉ ንቁ የሆርሞን አመንጪ አካል መሆናቸው በቅርቡ በተደረገ ሳይንሳዊ ጥናት ተረጋገጠ። በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ በዶክተር ጄራርድ ካርሰንቲ የተመራው የምርምር ቡድን እንዳመለከተው፣ እንደ መዝለል፣ መሮጥ እና ዳንስ ያሉ ጠንከር ያሉ እንቅስቃሴዎች አጥንቶች ኦስቲዮካልሲን (Osteocalcin) የተባለ ሆርሞን እንዲያመነጩ ያደርጋሉ።
ይህ በአጥንት የሚመነጨው ሆርሞን በደም ዝውውር አማካኝነት በቀጥታ ወደ ጭንቅላት በመጓዝ የመማር ብቃትን እና የማስታወስ ችሎታን በእጅጉ እንደሚያሳድግ በጥናቱ ተመልክቷል። በተለይም በእንስሳት ላይ በተደረገው ሙከራ ሆርሞኑ ትውስታን የማደስ ከፍተኛ አቅም እንዳለው የታየ ሲሆን፣ በሰዎች ላይ ግን እድሜ እየጨመረ ሲሄድ የዚህ ሆርሞን መጠን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንስ ተረጋግጧል።
ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት አጥንት ዝም ብሎ የቆመ መዋቅር ሳይሆን ከጭንቅላት ንቃት ጋር በቀጥታ የተገናኘ “የሆርሞን ፋብሪካ” ነው። በመሆኑም ሰውነትን የሚያንቀሳቅሱ ስፖርቶችን ማዘውተር አጥንትን ከማጠንከር ባለፈ፣ የአእምሮን ብቃት ለመጠበቅና የእርጅናን ተፅዕኖ ለመቀነስ ቁልፍ መፍትሔ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ አዲስ ግኝት በሕክምናው ዓለም ስለ አጥንትና ስለ ጭንቅላት ግንኙነት ያለውን ግንዛቤ የቀየረ ሲሆን፣ ወደፊት የመርሳት በሽታን ለመከላከል ለሚደረጉ ምርምሮች ትልቅ በር ከፋች እንደሚሆን ተስፋ ተጥሎበታል።
ማሳሰቢያ፦ ይህ መረጃ የቀረበው ለግንዛቤ ማስጨበጫ ብቻ ነው።
@seledadotio

No comments yet.