ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና ዢ ጂንፒንግ የሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ ዳግም እንዲከፈት ተስማሙ

- Advertisement -
Sidebar AD

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ የሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ (Strait of Hormuz) ዳግም መከፈት እንዳለበት መስማማታቸውን ዋይት ሃውስ አስታወቀ።

ሁለቱ መሪዎች ትናንት በነበራቸው ቆይታ በዓለም አቀፍ የንግድና የኃይል አቅርቦት ላይ ውይይት አድርገዋል።

በዚሁ ወቅት ቻይና ከመካከለኛው ምስራቅ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ያላትን ጥገኝነት ለመቀነስ፣ ከአሜሪካ ተጨማሪ የኃይል (ኢነርጂ) ምርቶችን የመግዛት ፍላጎት እንዳላት ገልጻለች።

ቤጂንግ ይህን እርምጃ ለመውሰድ ያሰበችው፣ ስልታዊ ጠቀሜታ ባለው የሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ ላይ የሚታየውን የእንቅስቃሴ መስተጓጎል ስጋት ለመቀነስ መሆኑ ተገልጿል።

ዋይት ሃውስ አክሎ እንደገለጸው፣ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ስምምነት በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ መረጋጋት ላይ አዎንታዊ ተፅእኖ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል ዘገባው የዋሽንግተን ፖስት ነው።

ልዑል ወልዴ



Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2