#Ethiopia | በዛሬው ዕለት በቻይና ሻንጋይ በተካሄደው የ2026 የዳይመንድ ሊግ መክፈቻ ውድድር ላይ የኢትዮጵያ አትሌቶች ደማቅና አስደናቂ ድሎችን አስመዝግበዋል።
በሴቶች 1500 ሜትር ውድድር አትሌት ብርቄ ኃየሎም 3:55.56 በሆነ ሰዓት በመግባት፣ የውድድሩን ክብረ-ወሰን በማሻሻል እና የወቅቱን የዓለም ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ በአንደኝነት አሸንፋለች።
በዚሁ ርቀት ላይ የተሳተፈችውና የፓሪስ ኦሎምፒክ የ800 ሜትር የብር ሜዳሊያ ባለቤቷ አትሌት ፅጌ 3:55.71 በመግባት የግል ምርጥ ሰዓቷን ስታሻሽል፣ ሌላኛዋ አትሌት ወርቅነሽ መሰለ ደግሞ 3:57.56 በሆነ ሰዓት 4ኛ ደረጃን በመያዝ የግሏን የዓመቱን ምርጥ ሰዓት ማስመዝገብ ችላለች።
በሴቶች 5000 ሜትር ውድድር ኬንያዊቷ አትሌት ፌይዝ ኪፕዬጎን አንደኛ ወጥታ ስታሸንፍ፣ የኢትዮጵያ አትሌቶች ግን ከ2ኛ እስከ 8ኛ ያለውን ደረጃ በበላይነት ተቆጣጥረውታል።
ከፌይዝ ጋር ጠንካራ ትንቅንቅ ያደረገችው አትሌት ልቅና አምባው 14:24.21 በሆነ የግል ምርጥ ሰዓቷ 2ኛ ደረጃን ስትይዝ፣ አትሌት ሰናይት ጌታቸው በበኩሏ 14:24.71 በሆነ ሌላ የግል ምርጥ ሰዓት 3ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሯን አጠናቃለች።
በሌላ በኩል፣ በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል ውድድር ዩጋንዳዊቷ ፔሩዝ በአንደኝነት ስታጠናቅቅ፣ አትሌት ኬና ቱፋ 8:59.66 በሆነ ሰዓት የግል ምርጥ ሰዓቷን በማስመዝገብ 4ኛ፣ እንዲሁም አትሌት ዓለምናት ዋለ 9:10.05 በመግባት 5ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
ጀርመናዊው አትሌት መሐመድ አብዱላሂ ባሸነፈበት የወንዶች 3000 ሜትር ውድድር ላይ አትሌት ኩማ ግርማ 7:29.20 በሆነ የግል ምርጥ ሰዓት 9ኛ፣ አትሌት ጌትነት ዋለ 7:29.98 በመግባት 14ኛ፣ ንብረት ክንዴ 7:34.61 በመግባት 18ኛ፣ እና አትሌት አብዲሳ ፈይሳ 7:36.73 በሆነ የግል ምርጥ ሰዓት 19ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #EBC
Source: GetuTemesgen









No comments yet.