እፎይታ የንግድ ማዕከላት ሽያጭ ኤክስፖ ተከፈተ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​ካቮድ ኮሜሪሻል ሪል እስቴት ደረጃቸውን የጠበቁ የንግድ ማዕከላትን ሽያጭ
ኤክስፖ በዛሬው እለት በጊዮን ሆቴል አስጀምሯል።

ኩባንያው ዘመናዊ የንግድ ቦታዎችን ለነጋዴው ማኅበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብና የኪራይ ዋጋ ንረትን ለመቅረፍ ያለመ ሲሆን፣ ግንባታቸው የተጀመሩት ሦስቱ ፕሮጀክቶች በሚቀጥለው አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው ለደንበኞች እንደሚረከቡ ተገልጿል።

በአዲስ አበባ ከተማ ስትራቴጂካዊ ቦታዎች ላይ እየተገነቡ ያሉትን እነዚህን ማዕከላት አስመልክቶም ኩባንያው ልዩ የሽያጭ እና የቦታ ማስተዋወቂያ ኤክስፖ መርሃ ግብር በግዮን ሆቴል አዘጋጅቷል።

​እነዚህ በግንባታ ላይ ያሉ የንግድ ማዕከላት በከተማዋ እምብርት እና ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ በሚታይባቸው ሽሮሜዳ፣ካሳንቺስ እና መገናኛ ባሉ ምቹ አካባቢዎች ላይ የሚገኙ በመሆናቸው ለንግድ ማኅበረሰቡ ተመራጭ ያደርጋቸዋል።

ማዕከላቱ በቴክኖሎጂ የተደገፉ ሰፊ የከርሰ ምድር የመኪና ማቆሚያዎች፣ የአውቶቡስ እና የታክሲ ተርሚናሎች ያሏቸው ሲሆን፣ ለአብነትም በሽሮሜዳ አካባቢ የሚገነባው ህንፃ “ጥበብ ሞል” በሚል ስያሜ የሚታወቅና አምስት የከርሰ ምድር ወለሎች ያሉት ነው።

በተመሳሳይ መልኩ በመገናኛ አካባቢ የሚገነባው ማዕከል “ካር ሞል” በሚል ስያሜ የሚጠራ ሲሆን፣ ዘመናዊ የአውቶቢስና ታክሲ ማቆሚያዎችን አካትተው የተዘጋጁ መሆናቸው በመርሐግብሩ ተገልጿል።

​የእነዚህ ፕሮጀክቶች ሌላው ልዩ ባህሪ ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን በአንድ ጣሪያ ስር ማቅረብ መቻላቸው ሲሆን፣ “ጥበብ ሞል” የኢትዮጵያን የባህልና የእደ ጥበብ ውጤቶች በስፋት የሚያስተዋውቅበት የራሱ የሆነ ራዕይ ያለው ህንፃ ሆኖ ተቀርጿል።

ከዚህም በተጨማሪ ማዕከላቱ ከንግድ ቦታዎች ባለፈ ለቤተሰብ መዝናኛነት የሚያገለግሉ የተለያዩ ዘመናዊ መናፈሻዎችንና መዝናኛ ቦታዎችን ያካተቱ በመሆናቸው ለገዢዎችም ሆነ ለጎብኝዎች ልዩ ምቾትን የሚሰጡ ናቸው።

ግንባታቸው በተጨባጭ እየተከናወነ የሚገኘው እነዚህ ማዕከላት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸው በዘርፉ ላይ የሚታየውን የቦታ እጥረት በከፍተኛ ደረጃ ያቃልላል ተብሎ ይጠበቃል።

​ካቮድ የንግድ ማኅበረሰቡን አቅም ባገናዘበ መልኩ ምቹና የረጅም ጊዜ የክፍያ ሥርዓት የዘረጋ ሲሆን፣ ደንበኞች በቅድሚያ 10 በመቶ ብቻ በመክፈል ቀሪውን ክፍያ በሒደት ማጠናቀቅ የሚችሉበት ዕድል ተመቻችቷል።

ኩባንያው በግዮን ሆቴል ባዘጋጀው መርሃ ግብር ላይ ለሚሳተፉና የንግድ ቦታዎችን ለሚገዙ ደንበኞች እስከ 40 በመቶ የሚደርስ ከፍተኛ የዋጋ ቅናሽ እና ከአምስት በላይ የተለያዩ የክፍያ አማራጮችን አቅርቧል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu #ጌጡ






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2