#Ethiopia | የአፍሪካ በሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ ክፍል በሚገኘው ኢቱሪ በተባለው አካባቢ የኢቦላ ወረርሽኝ በድጋሚ መቀስቀሱን አስታውቋል።
ማዕከሉ ባወጣው መረጃ መሰረት እስካሁን ድረስ 246 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን፣ የ65 ሰዎች ህይወት ደግሞ ለህልፈት ተዳርጓል። አብዛኛዎቹ ሟቾች ወርቅ ማውጫ በሆኑት ሞንግዋሉ እና ርዋምፓራ በተሰኙ መለስተኛ ከተሞች የተመዘገቡ መሆናቸውን የቢቢሲ ዘገባ አመላክቷል።
ቫይረሱ ከሰው ወደ ሰው በሰውነት ንክኪ እና በተጎዳ ቆዳ በሚገባ የሰውነት ፈሳሽ የሚተላለፍ ሲሆን፣ በበሽታው የተያዘ ሰው የመሞት እድሉ 50 በመቶ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ገልጿል።
ወረርሽኙን ለመግታትም የአፍሪካ በሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል ከኮንጎ፣ ርዋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን እና ከሌሎች ዓለም አቀፍ አጋር አካላት ጋር አስቸኳይ ምክክር ለማድረግ እየተዘጋጀ ይገኛል።
ይህ አደገኛ ወረርሽኝ በፈረንጆቹ 1976 ከተገኘበት ጊዜ ጀምሮ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሲከሰት የአሁኑ ለ17ኛ ጊዜ መሆኑ ተመዝግቧል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#ኢቦላ #ኮንጎ #የጤናወረርሽኝ #አፍሪካ #የአፍሪካበሽታመከላከያ #የአለምጤናድርጅት
Source: GetuTemesgen









No comments yet.