ለ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ አሁን በተከናወነው የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ድልድል ስነ-ስርዓት፣ የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን የወደፊት ተጋጣሚዎቹ እነማን እንደሆኑ ታውቋል።

በወጣው በዚህ ድልድል መሰረት ዋልያዎቹ በምድብ አስር ውስጥ የተመደቡ ሲሆን፣ ለዋናው ውድድር ለመብቃት ከሴኔጋል፣ ሱዳን እንዲሁም ከሞዛምቢክ ብሔራዊ ቡድኖች ጋር ከባድ ፉክክር ይጠብቃቸዋል።

የ2027ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር በምስራቅ አፍሪካዎቹ ጎረቤት ሀገራት በኬንያ፣ ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ አስተናጋጅነት እንደሚካሄድ በድጋሚ የተገለጸ ሲሆን የማጣሪያ ጨዋታዎቹም በመስከረም፣ በህዳር እና በመጋቢት ወራት በሚኖሩት የዓለም አቀፍ የእረፍት ቀናት እንደሚከናወኑ የወጣው መርሃ-ግብር ያሳያል።

#የአፍሪካዋንጫ #የምድብድልድል #ዋልያዎቹ #እግርኳስ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1