«ወደ ሥልጣን እንዲመለስ ከተባለዉ ዉሳኔ ጀርባ ያሉት ከ 100 የማይበልጡ ናቸዉ» ሳሞራ ዩኑስ

- Advertisement -
Sidebar AD

የቀድሞው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሳሞራ ዩኑስ በትግራይ ክልል ህወሓትን ወደ ስልጣን ለመመለስ የተደረገዉን ውሳኔ አጥብቀዉ ተቃወሙ። በዚህ ሳምንት ከውጋሕት ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “የቀድሞ አመራሮች እና ምክር ቤት (በትግራይ) ወደነበሩበት እንዲመለሱ መወሰኑ ህዝቡን ከልክ በላይ ጭንቀት ውስጥ ከቶታል „ብለዋል። ሳሞራ የህወሓት ነባር ታጋይና አባልም ነበሩ።

ሳሞራ አክለውም የትግራይ ህዝብ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የግል ንብረት ስላልሆነ በፓርቲው ታግቶ መቀመጥ የለበትም ሲሉም አክለዋል። ከጦርነቱ በፊት የነበረው የክልል ምክር ቤትና አስተዳደር «ወደ ሥልጣን እንዲመለስ ከተባለዉ ዉሳኔ ጀርባ ያሉት ከ 100 የማይበልጡ ናቸዉ፣ ውሳኔዉን ያሳለፉትም ከተጠያቂነት ለመዳን ያሰበ ዓላማን የያዘ ነዉ» ብለዉ እንደሚያስቡ ሳሞራ ዩንስ ተናግረዋል።

DW Amharic




Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1