#Ethiopia | በአሜሪካ በሚቺጋን ሎውረንስ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ በተካሄደው የ2026 የሮቦፌስት ዓለም አቀፍ የታዳጊዎች የሮቦቲክስ እና ሰው ሰራሽ አስተውህሎት ሻምፒዮና ላይ የኢትዮጵያ ተወካይ ቡድን ደማቅ ስኬት አስመዝግቧል።
ቡድኑ እንደ ታይዋን፣ ደቡብ ኮሪያ እና ቻይና ካሉ በቴክኖሎጂ የበለጸጉ 39 አገራት እና በዓለም ዙሪያ ከተወዳደሩ 738 ቡድኖች ጋር ብርቱ ፉክክር በማድረግ የሚከተሉትን ከፍተኛ ውጤቶች አግኝቷል።
በሕክምና ሮቦቲክስ የሕዝብ ምርጫ ዘርፍ አንደኛ ደረጃ፣
በሕክምና ሮቦቲክስ ዋናው የውድድር ክፍል አምስተኛ ደረጃ፣
በፈጠራ ሥራዎች ማሳያ ዘርፍ ስድስተኛ ደረጃ፣
ይህ ስኬት ከመመዝገቡ ከአንድ ወር በፊት በግሪክ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የሚኖአን ሮቦቲክስ ሻምፒዮና ላይ ሌላው የኢትዮጵያ የታዳጊዎች ቡድን ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል።
እነዚህ ተከታታይ ውጤቶች የታዳጊዎቻችንን ዓለም አቀፍ ብቃት እና ትጋት ከማሳየታቸውም በላይ አገራችን በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያላትን ብሩህ ተስፋ የሚያረጋግጡ ናቸው።
#Robofest2026 #Robotics #AI #EthiopianYouth #Technology #STEM #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen









No comments yet.