ለሴት አስተናጋጆች የወጣው አለባበስን የሚመለከተው ደንብ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እየተደረገ እንዳልሆነ ተገለጸ

- Advertisement -
Sidebar AD

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሴት አስተናጋጆች የተጋለጠ አለባበስ እንዳይለብሱ ለመከልከል ያወጣው ደንብ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እየተደረገ እንዳልሆነ የኢትዮጵያ መስተንግዶ ባለሙያዎች ማኅበር ለአሐዱ አስታውቋል።

ማኅበሩ ለአሐዱ እንዳስታወቀው፤ የከተማ አስተዳደሩ የደንብ ልብስ አለባበስና አፈጻጸም ደንብ ቁጥር 178/2016ትን ተግባራዊ ካደረገ በኋላ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ለውጥ ቢታይም፣ በአንዳንድ ተቋማት አሁንም ሴት አስተናጋጆች ስራቸውን ሲሰሩ ሰውነታቸውን የሚያጋልጥ አጭር ቀሚስ እንዲለብሱ መገደዳቸው ቀጥሏል።

በተለይ በምሽት አገልግሎቶች አስተናጋጆች ደንበኛን ለመሳብ በጣም አጫጭር ቀሚሶችን እንዲለብሱ ይገደዳሉ ያሉት የማኅበሩ ፕሬዚዳንት አቶ ያሬድ ደገፉ፤ ደንቡ ጸድቆ ስራ ላይ ከዋለ በኋላ የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ለባለሙያዎች እና ለሆቴል ባለቤቶች ተከታታይ ሥልጠናዎች መስጠቱን አስታውሰው፤ አብዛኛዎቹ የሥራ ኃላፊዎች የደንቡን ድንጋጌዎች በመረዳታቸው መሻሻሎች ታይተዋል ብለዋል፡፡

ለችግሩ እንደ መፍትሔ ከቀረቡት አማራጮች መካከል ባህላዊ ሬስቶራንቶች ውስጥ ያሉ አስተናጋጆች ሙሉ የሀበሻ ልብስ እንዲለብሱ ማድረግ እንደሆነም ተነስቷል፡፡ ደንበኞች የቤት መምረጫ መስፈርታቸው የአገልግሎት ጥራት እንዲሆንም አቶ ያሬድ አሳስበዋል፡፡

በመስተንግዶ ዘርፍ ያሉ ባለሙያዎች መብታቸውን፣ ደመወዛቸውንና የአለባበስ ነፃነታቸውን ለማስከበር በማኅበር ተደራጅተው እንዲንቀሳቀሱም ጥሪ አቅርበዋል።

#አሐዱ


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: