የማንቸስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ እሁድ ከአስቶን ቪላ ጋር ከሚያደርጉት የውድድር ዘመኑ የመጨረሻ ጨዋታ በኋላ ክለቡን እንደሚለቁ ተነገረ
በፈረንጆቹ 2016 ክለቡን የተቀላቀሉት ስፔናዊው አሰልጣኝ፣ በኢትሃድ ስታዲየም ባሳለፏቸው 10 ስኬታማ ዓመታት ውስጥ 6 የፕሪሚየር ሊግ እና 1 የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 20 ዋና ዋና ዋንጫዎችን በማንሳት የክለቡ ታሪክ ስኬታማው አሰልጣኝ መሆን ችለዋል።
ጋርዲዮላ በሰጡት መግለጫ “የምለቅበትን ምክንያት አትጠይቁኝ፤ ነገር ግን ጊዜዬ እንደበቃ በውስጤ አውቀዋለሁ፤ ዘላለማዊ የሚሆን ነገር የለም” ብለዋል።
አርሰናል የዘንድሮውን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ማሸነፉን ተከትሎ የመጣው ይህ ውሳኔ የስፖርቱን ዓለም አስደንግጧል።
ጋርዲዮላ ከክለቡ ቢለቁም በሲቲ ፉትቦል ግሩፕ (CFG) ውስጥ በዓለም አቀፍ አምባሳደርነት ሥራቸውን እንደሚቀጥሉ ታውቋል።
እሳቸውን ለመተካት የቀድሞው የቼልሲ አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ ቀዳሚ እጩ ሆነዋል።
ምንጭ፦ BBC
@seledadotio

No comments yet.