የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የናፍጣ ዋጋ እንዲቀንስ ትዕዛዝ አስተላለፉ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በአሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን ጋር እያደረጉት ባለው ጦርነት ምክንያት የነዳጅ ዋጋ በመናሩ የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞና የትራንስፖርት አድማ ተከትሎ፣ የናፍጣ ዋጋ እንዲቀንስ መንግስታቸው መወሰኑን አስታውቀዋል። ፕሬዝዳንቱ ዛሬ ከሀገሪቱ የትራንስፖርት ዘርፍ ተዋናዮች ጋር ከተወያዩ በኋላ በሰጡት መግለጫ፣ በቅርቡ በሚወጣው የሰኔ እና ሐምሌ ወራት የዋጋ ክለሳ ላይ በአንድ ሊትር ናፍጣ ላይ የ10 የኬንያ ሺሊንግ ቅናሽ እንዲደረግ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።

​በመካከለኛው ምስራቅ በተቀሰቀሰው ጦርነት እና የሆርሙዝ ሰርጥ መዘጋትን ተከትሎ በኬንያ የናፍጣ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮ የነበረ ሲሆን፣ ይህም በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ በሀገሪቱ የተቀሰቀሰ ከፍተኛ የትራንስፖርት መዘጋት እና የሰዎች ህይወት የጠፋበት ተቃውሞ አስከትሏል። መንግስት የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት ካለፉት ሁለት ወራት ወዲህ ከ28 ቢሊዮን ሺሊንግ በላይ በድጎማ እና በታክስ ቅናሽ መልክ ወጪ ማድረጉን ፕሬዝዳንት ሩቶ ገልጸዋል። ይህ አዲሱ የዋጋ ቅናሽ ውሳኔ በሀገሪቱ ተፈጥሮ የነበረውን የትራንስፖርት አድማ ለማርገብ የተወሰነ መሆኑ ተገልጿል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2