ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የወርቅ ጌጣጌጦች የሰረቀው ተጠርጣሪ በፈጣን ክትትል በቁጥጥር ስር ዋለ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ዘርፌ ቦኖ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ጎረቤቶቹ ወደ እምነት ተቋም ማምራታቸውን የተገነዘበው ተጠርጣሪው ዮሐንስ ወንድወሰን፣ ተመሳሳይ ቁልፍ በመጠቀም ወደ መኖሪያ ቤታቸው በመግባት ከፍተኛ የስርቆት ወንጀል ፈጽሟል።

ግለሰቡ በቤቱ ውስጥ የነበረን ኮሞዲኖ በመስበር 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ሁለት የአንገት ሰንሰለቶችና ሁለት የእጅ አንባሮች፣ የ240 ሺህ ብር የጆሮ ጌጥ እንዲሁም 170 የአሜሪካ ዶላር በድምሩ 2,201,500 ብር ግምት ያላቸውን ንብረቶች ሰርቆ ተሰውሮ እንደነበር የኮተቤ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ገልጧል።

ተበዳዩ ወዲያውኑ ድርጊቱን ለህግ አስከባሪዎች ማመልከታቸውን ተከትሎ፣ የፖሊስ መርማሪዎች ባደረጉት አስቸኳይ ክትትልና ፍለጋ ወንጀሉ በተፈጸመ በ12 ሰዓታት ውስጥ ተጠርጣሪውን መያዝ ተችሏል።

ግለሰቡ ሰርቆት በምስጢር በኮንቴነር ውስጥ ደብቆት የነበረው የወርቅ ጌጣጌጥና ጥሬ ገንዘብም ሙሉ በሙሉ ተገኝቷል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ህብረተሰቡ መሰል የወንጀል ድርጊቶች ሲከሰቱ ፈጣን ጥቆማ በመስጠት እያደረገ ያለው ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክቱን አስተላልፏል።

#AddisPolice #CrimeNews #Yeka #GoldTheft #BreakingNews #PoliceChases #AddisAbabaCity #SecurityUpdate #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: