የኢትዮጲያ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ አርሰናልን ጨምሮ የአውሮፓ ክለቦችን ለምርጫ ቅስቀሳነት ተጠቀሙ!
ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ተመስገን ጥሩነህ ትላንት በባህርዳር ስቴዲየም በምርጫ ቅስቀሳ መረሀግብር ላይ በዚህ የባህርዳር ስቴዲየም እነ አርሰናል ማንቺስተር ቼልሲ ሊቨርፑ ባርሳ ቫሌንሺያአምጥተን ማጫወት እንፈልጋለን ሲሉ የአውሮፓ ክለቦችን ለምራጫ ቅስቀሳ መጠቀማቸው ተነግሯል።
ፖለቲከኞች የወጣቱን ሙቀት እየለኩ በወጣቱ ስሜት የበሬ ወለደ ንግግር ትርፍ ለማግኘት ሲሞክሩ በጣም አስቂኝ ነው። ወጣቱ ከሰሞኑ በኳስ እንዲህ ሲደሰት ያያችሁት በሀገሪቷ ያለውን ምስቅልቅል ረስቶ አይደለም ስራ ማጣቱንም ዘንግቶ አይደለም ፤
በጥቅሉ በሀገሪቱ ያለውን ችግር ረስቶ ሳይሆን እግርኳስ ከችግሮቹ ርቆ የሚደሰትበት አንዱ አማራጩ ስለሆነ ነው። ስለዚህ የበሬ ወለደ ወሬ ትታችሁ ለወጣቱ የሚሆን መፍትሄ ፈልጉ። ወጣቱ ዝምታን መምረጡ የናንተ ማላገጫ እንዲሆን ፈቅዶላችሀኋል ግን ተረጋጉ
የፓርቲያችሁ ርዕዮተ አለም የሀገሪቷ ችግር ላይ ያተኩር እንጂ ወጣቱን ላሞኘው የሚል አይሁን እኛ ጅል አይደለንም።
የሕዝብ ሕልውና ማስጠበቅ ፣ የአገር ሉዓላዊነትን ማስከበር፣ በጋራ ዕሴቶች ላይ የተመሰረተ ብሄራዊ አንድነትን ማጽናት እና ለሁሉም ዜጋ እኩል እድል የሚሰጥ የፍትሕ ስርዓትን መገንባት የሚሉ ርዕዮተ አለማዊ መርሆዎች ሊኖራችሁ ሲገባ በንደዚህ ተራ ነገር የወጣቱን ቀልብ ልሳብ ተብሎ አይሞከርም። ስንት የቤት ስራ ተከምሮባችሁ ጨረቃ ላይ ስለማውጣት አትንገሩን ወጣቱ ስለሀገሩ የማይጨነቅ አይመሰላችሁ!
የሕዝብ ንቃተ – ሕሊና ላይ የሚረማመዱበት መጠን በቃል አይገለፅም። በነገራችን ላይ ይሄ ፖለቲካ አይደለም ወጣቱ ሲናገር ምክር ስሙ የኛን ክለብ የወጣቱ ልብ ውስጥ ለመግቢያ በውሸት እና በህልም እንጀራ አትጠቀሙት!
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.