በኢትዮጵያ ዋንጫ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን በሲዳማ ቡና በመለያ ምት በተረታበት መርሀግብሩ 33ኛው ደቂቃ ላይ ተቀይሮ ሲወጣ መለያን አውልቆ በአሰልጣኝ ገብረመድኅን ሐይሌ ፊት የጣለው እና ከቡድን መሪው መስፍን አህመድ ጋር በገባው እሰጣገባ በበርካቶች ዘንድ መነጋገሪያ የነበረው ወጣቱ የግራ መስመር ተከላካይ ያሬድ ካሳዬ ከክለቡ ካንፕ እንዲሰናበት መደረጉን ሀትሪክ ስፖርት ለማወቅ ችላለች።
ከማላዊ ብሔራዊ ቡድን ጋር ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ ቀናት የወዳጅነት ጨዋታ ያላት ሲሆን የዋልያዎቹ አለቃ ዮሐንስ ሳህሌ ተጫዋቹን በስብሰባቸው ውስጥ ማካተት ያልቻሉትም በዚሁ የትላንቱ ጉዳይ ስለመሆኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
መረጃው የሃትሪክ ስፖርት ነው
Source: FastMereja








No comments yet.