ኮሜርሺያል ኖሚኒስ ዘመናዊ የሥልጠና ማዕከሉን አስመረቀ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Fastmereja:በሀገራችን የአውትሶርሲንግ እና የሦስተኛ ወገን አገልግሎት ዘርፍ ቀዳሚ የሆነው ኮሜርሺያል ኖሚኒስ የተመሰረተበትን 60ኛ ዓመት አልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል እያከበረ ባለበት በዚህ ዓመት፣ የአገልግሎት ጥራትንና የሰው ኃይል ሙያዊ ክህሎትን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ዘመናዊ የሥልጠና ማዕከል በዛሬዉ እለት አስመረቀ።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የኮሜርሺያል ኖሚኒስ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢንተርናሽናል ባንኪንግ ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ዮናስ ልደቱ፣ የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ካሳሁን ፎሎ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የባለድርሻ አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው ክቡራን እንግዶች ተገኝተዋል።

ዛሬ የተመረቀውና በጠቅላላው 1,400 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ ያረፈው አዲሱ የሥልጠና ማዕከል፤ በአጠቃላይ 580 ካሬ ሜትር የወለል ስፋት ያላቸውን አንድ ባለ G+4፣ አንድ ባለ G+2 እና አንድ ባለ G+1 ዘመናዊ ሕንፃዎችን በውስጡ ያካተተ ነው።

ማዕከሉ ዘመናዊ የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ ሰፋፊ የሥልጠና ክፍሎች፣ ካፌቴሪያ፣ የላውንደሪ አገልግሎት መስጫ፣ እንዲሁም ለተግባራዊ ሥልጠና የሚውሉ የጽዳት ዕቃዎችና ማሽነሪዎች ማሳያ ክፍሎችን (Showrooms) ይዟል።

ከዚህ በተጨማሪም አስተማማኝ የደኅንነት ጥበቃ ሥርዓት፣ የመጠባበቂያ ጄኔሬተር፣ ከፍተኛ የዋይፋይ ኢንተርኔትና ዘመናዊ የድምፅና ፕሮጀክተር መሣሪያዎች የተሟሉለት ቀዳሚ የልህቀት ማዕከል (Center of Excellence) መሆኑ ተገልጿል።

ይህ የሥልጠና ማዕከል በቴክኒክ ክህሎት ላይ ብቻ ሳይገደብ፤ በሥነ-ምግባር፣ በሥነ-ሥርዓት፣ በደንበኛ አያያዝ፣ በደኅንነት ሳይንስ (Security Science) እና በአመራር ብቃት ላይ ያተኮሩ ሁለንተናዊ የአጭርና የመካከለኛ ጊዜ ሥልጠናዎችን በጥራት ለመስጠት የተደራጀ መሆኑ ነዉ የተገለፀዉ።

ማዕከሉ ለኮሜርሺያል ኖሚኒስ ሠራተኞች ብቻ ሳይሆን፤ ለተለያዩ የመንግሥትና መንግሥታዊ ላልሆኑ ተቋማት፣ ለግል ድርጅቶች፣ በተለይም ደግሞ በሰርቪስ (አገልግሎት) ሴክተር ላይ ለተሰማሩ ባለድርሻ አካላትና ክቡራን ደንበኞች በሙሉ ክፍት መሆኑ ታውቋል።

ተቋሙ የሰው ኃይልን ወደ ላቀ ሙያዊ ብቃት በመቀየር ረገድ ያለውን ቁርጠኝነት በመግለጽ፣ ሁሉም አጋር ድርጅቶች የዚህን ማዕከል ሁለንተናዊ የሥልጠና ዕድሎች በጋራ እንዲጠቀሙበት ጥሪውን አስተላልፏል።

ተቋሙ ለ60 ዓመታት በታማኝነት ያቀረባቸውን ከ13 በላይ የሆኑ የሦስተኛ ወገን አገልግሎቶች ዓይነት፣ ስብጥር እና ጥራት ከፍ በማድረግ፣ ከሀገራችን አልፎ በአፍሪካ ደረጃ ተወዳዳሪ እና ተመራጭ ኩባንያ ሆኖ ለመውጣት በስትራቴጂክ ግቦቹ ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሠራ አስታውቋል።

ኮሜርሺያል ኖሚኒስ በአሁኑ ወቅት በመላው የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ 32 ቅርንጫፎቹ አማካኝነት ከ 40 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ዘላቂ የሥራ ዕድል መፍጠርየቻለ ሲሆን፣ በየዓመቱ ገቢውን በማሳደግና በታማኝ ግብር ከፋይነቱ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ እጅ በተከታታይ ሽልማቶችን የተቀበለ ግዙፍ ተቋም ነዉ።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2