የኢራን አብዮታዊ ዘብ በአጸፋ እርምጃ ‘የአሜሪካ አየር ኃይል ሰፈርን’ መምታቱን አስታወቀአሜሪካ የፈጸመችው ጥቃት ተከትሎ የኢራ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የኢራን አብዮታዊ ዘብ በአጸፋ እርምጃ ‘የአሜሪካ አየር ኃይል ሰፈርን’ መምታቱን አስታወቀ‼️
አሜሪካ የፈጸመችው ጥቃት ተከትሎ የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ወሰድኩት ባለው የአጸፋ እርምጃ “የአሜሪካ አየር ኃይል ሰፈርን” መምታቱን አስታወቀ።
አሜሪካ ሌሊት ላይ በኢራን የወደብ ከተማ ባንዳር አባስ ውስጥ በሚገኝ የአውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ ለአየር እና ለባሕር ኃይሏ ስጋት እንደሆኑ የገለጸቻቸውን ወታደራዊ ማዕከላት መምታቷን አስታውቃለች።
የኢራን አብዮታዊ ዘብ ጥቃቱ ምንም ጉዳት እንዳላደረሰ በመጥቀስ በምላሹ የአሜሪካ የወረራ ጥቃት መነሻ ነው ባለው የአየር ኃይል ሰፈር ላይ ጥቃት መፈጸሙን የኢራን ዜና ወኪል ታስኒም ይዞት በወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል።
ይህ ጥቃት የተፈጸመበት ወታደራዊ ማዕከል የት እንደሚገኝ ግን በትክክል አልተገለጸም።
የአብዮታዊ ዘቡ ጨምሮም “የጠብ ጫሪነት ጥቃቶች አጸፋ እንደሚሰጣቸው” በማመልከት ጥቃቶች የሚቀጥሉ ከሆነ “የበለጠ ከባድ” ምላሽ እንደሚኖር ገልጿል።
ከአብዮታዊ ዘቡ ጋር ቅርብ የሆነው ታስኒም የዜና ወኪል ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው አሜሪካ ሌሊት ላይ የፈጸመችው ጥቃት ምንም ነገር በሌለበት ቦታ ላይ መሆኑን እና ፍንዳታውም የተሰማው ከዚያ ጋር የተያያዘ መሆኑን አመልክቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢራን አብዮታዊ ዘብ በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የራዳር መከታተያውን አጥፍቶ ሊያልፍ የነበረ የአሜሪካ ነዳጅ ጫኝ መርከብን ማስቆሙን ታስኒም የዜና ወኪል ዘግቧል።
ዘገባው እንዳመለከተው የአብዮታዊ ዘቡ ባሕር ኃይል በመርከቡ ላይ ተኩስ ከፍቶ ወደ መጣበት እንዲመለስ ማስገደዱንም ገልጿል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: