የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዲጂታል መተግበሪያው ላይ የገጠመውን መስተጓጎል ለመፍታት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#Ethiopia | የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቅርቡ ባደረገው የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ (Mobile Banking App) ማሻሻያ ምክንያት በተወሰኑ ደንበኞች ላይ የአገልግሎት መስተጓጎል ማጋጠሙን ጠቅሶ፣ ችግሩን በአፋጣኝ ለመፍታት ርብርብ እያደረገ መሆኑን ገለጸ።

​ባንኩ ለአገልግሎት ምቹና በርካታ አዳዲስ አማራጮችን ያካተተ የተሻሻለ መተግበሪያ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ፣ በርካታ ደንበኞች እየተጠቀሙበት ቢሆንም፣ አዲስ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በአንዳንድ ተጠቃሚዎች ላይ መስተጓጎል መታየቱን አስታውቋል።

​ባንኩ ለተፈጠረው መስተጓጎል ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን፣ ችግሩ ሙሉ በሙሉ ተፈቶ ሲጠናቀቅ ለደንበኞቹ በይፋ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

​ከተሻሻለው መተግበሪያ ጋር በተያያዘ ችግር ያጋጠማቸው ደንበኞች በሚከተሉት አማራጮች እገዛ እና ድጋፍ ማግኘት እንደሚችሉ ባንኩ ጠቁሟል፡

​በነፃ የጥሪ ማዕከል: ወደ 951 በመደወል፣
​በዲጂታል አማራጭ: በባንኩ ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጾች መልዕክት በመላክ፣
​በቀጥታ ሊንክ: ባንኩ ባዘጋጀው የድጋፍ መስጫ ማስፈንጠሪያ (Link) በመጠቀም።

https://chat.whatsapp.com/BFR1h7SrAti091qznFEP4u

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
​#የኢትዮጵያንግድባንክ #CBE
#ዲጂታልባንኪንግ #የሞባይልባንኪንግ #የደንበኞችአገልግሎት #የቴክኖሎጂማሻሻያ


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2