በኬንያ በሚገኝ አንድ የሴቶች ትምህርት ቤት ውስጥ 16 ተማሪዎችን ለህልፈት ለዳረገው እና ሆን ተብሎ ለተለኮሰ እሳት እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩ ስምንት ተማሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታውቋል።
ከዋና ከተማዋ ናይሮቢ በስተሰሜን ምዕራብ 120 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ጊልጊል ከተማ በሚገኘው የኡቱሚሺ ሴቶች አካዳሚ ሐሙስ ማለዳ የተቀሰቀሰው እሳት 1መቶ35 ተደራራቢ አልጋዎች የነበሩበትን የመኝታ ክፍል የላይኛውን ፎቅ ሙሉ በሙሉ አውድሞታል።
የብሔራዊ ፖሊስ አገልግሎት ባወጣው መግለጫ፤ ከተማሪዎችና ከሰራተኞች ጋር ከተደረጉ ቃለ-መጠይቆች እንዲሁም የቪዲዮ ካሜራ ምስሎችን በፎረንሲክ ከመረመረ በኋላ፣ ስምንት የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ከእሳቱ ‹‹ዕቅድ እና አፈጻጸም ጋር በተያያዘ ተፈላጊ ግለሰቦች›› መሆናቸውን መለየቱን ገልጿል።
የቃጠሎውን ትክክለኛ መንስኤ ለማወቅ ምርመራው አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡
ፖሊስ እንዳለው ተማሪዎቹ በክትትል ከተገኙ በኋላ ለጥያቄ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፤ ወደ ትምህርት ቤቱ እንዲመለሱ ተደርጓል በዚያው አካባቢ የነበሩ ሌሎች ተማሪዎችም ተለይተው በቁጥጥር ስር ውለዋል ነዉ የተባለዉ።
እነዚህ ስምንት ተማሪዎች ገዳዩን የእሳት አደጋ በሚመረምሩ መርማሪዎች መጀመሪያ ላይ ተለይተው ወደ ትምህርት ቤቱ እንዲመለሱ ከተደረጉት 30 ተማሪዎች መካከል የሚገኙ ናቸው።
ኬንያ በትምህርት ቤቶች የእሳት አደጋ ረጅም ታሪክ ያላት ሲሆን፤ ከሁለት ዓመት በፊት እንኳ በማዕከላዊ ኬንያ በሚገኝ የአዳሪ ትምህርት ቤት የመኝታ ክፍል ውስጥ በተነሳ እሳት ቢያንስ 21 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።
በአዳሪ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚከሰቱ በርካታ የቃጠሎ አደጋዎች ሆን ተብሎ በሚለኮስ እሳት ምክንያት የሚፈጠሩ ሲሆን፤ በትምህርት ቤቱ ዲሲፕሊንና የአኗኗር ሁኔታ ያልተደሰቱ ተማሪዎች ለዚህ ተጠያቂ ተደርገዉ ይከሰሳሉ።
ሀና ሰይፉ
Source: Yeneta Tube








No comments yet.