የወንድ ወታደሮች እጥረት በኔቶ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ከፈረንጆቹ የካቲት 2022 ከሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት መባባስ ወዲህ የኔቶ አባላት የሩሲያን ስጋት እንደ ምክንያት በመጥቀስ ከፍተኛ የወታደራዊ ግንባታ ቢያካሂዱም ሞስኮ ግን መሰረተ ቢስ ስጋት በማለት ውድቅ አድርጋዋለች።

በርካታ ሀገራት የግዴታ ውትድርናን በድጋሚ የጀመሩ ሲሆን፣ ሌሎች ደግሞ ሴቶችን ለውትድርና ምልመላ ማጨት መጀመራቸው ተሰምቷል።

ይህንን ስጋት ተከትሎ በኢስቶኒያ ሴቶችን በግዴታ ለውትድርና መመልመል አይቀሬ መሆኑን የሀገሪቱ የመከላከያ ተቋም አስታውቋል፡፡

ከሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት በኋላ በርካታ የኔቶ አባል ሀገራት የጾታ ልዩነት የሌለበት የውትድርና አገልግሎት ምልመላን ተግባራዊ እያደረጉ ይገኛሉ።

በፈረንጆቹ በ2015 ኖርዌይ ለሴቶች የግዴታ ወታደራዊ አገልግሎትን በማስተዋወቅ የመጀመሪያዋ የጥምረቱ አባል ሀገር ስትሆን፣ ስዊድን በ2017 ተከትላለች።

በሌላ በኩል ኔዘርላንድስ በ2018 የምልመላ ደንቧን ወደ ሴቶች ያሰፋች ቢሆንም፣ በሰላም ጊዜ ረቂቅ ደንቡ ታግዶ እንደሚቆይ ህግ ማውጣቷ ይታወሳል፡፡ አር ቲ እንደዘገበው ፡፡

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
#nbc #NATO #usa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: