የዶናልድ ትራምፕ የጤና ምርመራ ውጤት ይፋ ሆነ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዎልተር ሪድ ወታደራዊ የህክምና ማዕከል ያደረጉትን ዝርዝር የጤና ምርመራ ተከትሎ፣ የግል ሃኪማቸው ሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙና ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ብቁ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

​በ22 ስፔሻሊስቶች የተከናወነው ይህ ምርመራ እንደሚያሳየው፣ ትራምፕ 108 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ ሲሆን የሰውነት ብዛት ማውጫቸው (BMI) 29.7 ደርሷል።

ይህም ከመጠን ያለፈ ውፍረት ጠርዝ ላይ የሚያስቀምጣቸው በመሆኑ ሃኪሞች የአመጋገብና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማሻሻያ ጠቁመዋል።

​በእጆቻቸው ላይ የታዩ የመሰማበር ምልክቶች በአስፒሪን አጠቃቀም ምክንያት የመጡ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ የልብ፣ የሳንባ እና የነርቭ ምርመራዎቻቸው ግን መደበኛ ናቸው።

በተጨማሪም በትራምፕ ላይ የተደረገው የእውቀት ማስተዋል (cognitive) ፈተና ሙሉ ውጤት ያስመዘገበ ሲሆን፣ የኮሌስትሮል መጠናቸውም መሻሻል አሳይቷል።

እንደ ፊደል ፖስት ዘገባ እድሜያቸው ወደ 80 እየተቃረበ የመጣው ትራምፕ፣ የታሪክ አንጋፋው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ናቸው ።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: