#Ethiopia | የጃፓን ህዝብ ቁጥር ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ብቻ ከ3 ሚሊዮን በላይ እንደቀነሰ የመንግስት ይፋዊ ሪፖርት አመለከተ።
በሀገሪቱ የስነ-ህዝብ መረጃ መሰረት በ2020 ዓ.ም 126.1 ሚሊዮን የነበረው የህዝብ ቁጥር በ2025 ዓ.ም ወደ 123 ሚሊዮን ዝቅ ብሏል።
ይህ ታሪካዊ ማሽቆልቆል ጃፓን እ.ኤ.አ ከ1920 ጀምሮ የህዝብ ቆጠራ መመዝገብ ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።
ሀገሪቱ እ.ኤ.አ በ2008 ዓ.ም 128 ሚሊዮን በመድረስ ከፍተኛውን የህዝብ ቁጥር ያስመዘገበች ቢሆንም፥ አሁን ባለው አካሄድ እስከ 2070 ዓ.ም ድረስ ቁጥሩ ወደ 87 ሚሊዮን ሊወርድ እንደሚችል ተገምቷል።
የጃፓን መንግስት ወጣቶች ያለገደብ ልጅ እንዲወልዱ የተለያዩ ማበረታቻዎችን ቢያቀርብም፥ የኑሮ ውድነትና የማህበራዊ ህይወት ለውጦች ጥረቱን ፍሬ አልባ አድርገውታል።
አሁን ላይ በሀገሪቱ ያለው የውልደትና የሞት ምጣኔ እጅግ የተዛባ ሲሆን፥ በአማካይ አንድ ህጻን ሲወለድ በተቃራኒው የሁለት ሰዎች ህልፈት እየተመዘገበ ይገኛል።
ይህ እያገረሸ የመጣው የህዝብ ቁጥር መመናመን በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ላይ ከፍተኛ እንቅፋት መፍጠሩ ተነግሯል።
ከዚህም በተጨማሪ የሰራተኛ እጥረት እያስከተለ መሆኑ እና በጤናው ዘርፍ ላይ ከባድ ጫና እየጣለ እንደሚገኝ ብሄራዊ የስቴትስቲክስ ኤጀንሲው አስታውቋል።
የችግሩን አሳሳቢነት ይበልጥ ማሳያ የሚሆነው ከሀገሪቱ 47 ግዛቶች ውስጥ በሁለቱ ላይ ብቻ መጠነኛ መረጋጋት ሲታይ፥ በቀሪዎቹ 45 ግዛቶች ግን የህዝብ ቁጥር መቀነሱ በከፍተኛ ፍጥነት ቀጥሏል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#Japan #DemographicCrisis #JapanPopulation #GlobalNews #Economy #PopulationDecline #AsiaNews
Source: GetuTemesgen









No comments yet.