የፋይዳ መታወቂያ የተመዘገበን ስልክ ቁጥር በአካል እና በኢንተርኔት መቀየር የሚያስችል አሰራር መዘርጋቱ ተገለጸ
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የፋይዳ መታወቂያ ያወጡበት ስልክ ቁጥር በተለያየ ምክንያት እጃቸው ላይ የሌለ ዜጎች በሌላ ስልክ ቁጥር እንዲቀይሩ እድል የሚሰጥ አሰራር መኖሩን አስታውቋል።
አሰራሩ የተዘረጋው ፋይዳ መታወቂያ የወሰዱበትን ስልክ ቁጥር ማግኘት ባለመቻላቸው የባንክ ሂሳብ ማንቀሳቀስን ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶችን ማግኘት ለተቸገሩ ዜጎች ምላሽ ለመስጠት ነው ተብሏል።
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የባለድርሻ አካላት እና የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሳሚናስ ሰይፉ ለአሐዱ ሬድዮ እንደገለጹት፤ መረጃውን የምዝገባ ማሽኖች ባሉባቸው ጣቢያዎች በመገኘት ስልክ ቁጥር መቀየር እንደሚቻል ዳይሬክተሩ አብራርተዋል።
በአሁኑ ወቅት የበርካታ ሰዎች ስልክ ቁጥር፣ የስም እና የልደት ዘመን መረጃዎች በመሳሳታቸው ይስተካከልልን የሚል ጥያቄ በመቅረቡ የማስተካከል ስራ በስፋት እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።
መታወቂያቸው ላይ ያስመዘገቡትን ስልክ ቁጥር ማግኘት ለሚቸገሩ ዜጎች ሁለት አማራጮች መዘጋጀታቸውን ዳይሬክተሩ ለአሐዱ ገልጸዋል።
የመጀመሪያው አማራጭ ነዋሪዎች የቀድሞውን ስልክ ቁጥራቸውን ማግኘት የሚችሉ ከሆነ በራሳቸው የተቋሙ ድረ-ገጽ ውስጥ በመግባት መቀየር የሚችሉበት ነው ተብሏል።
ሁለተኛው አማራጭ ደግሞ የተመዘገቡበትን ስልክ ቁጥር ሙሉ በሙሉ ማግኘት ለማይችሉ ዜጎች የተዘጋጀ እንደሆነ ተገልጿል።
እነዚህ ወገኖች የፋይዳ ምዝገባ ማሽኖች ወደሚገኙባቸው ጣቢያዎች በአካል በመገኘት ማስተካከል እንደሚችሉ አቶ ሳሚናስ ሰይፉ አስታውቀዋል።
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.