ታዋቂዋ ማራቶን አትሌት ፋጡማ ሮባ እና ጋዜጠኛ ካሳሁን ፈይሳ ከዓመታት በኋላ በደስታ ተገናኙ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የኢትዮጵያን ስም በዓለም አደባባይ ካስጠሩ ስመ ጥር የስፖርት ባልባለቶች መካከል አንዷ የሆነችው አትሌት ፋጡማ ሮባ እና ጋዜጠኛ ካሳሁን ፈይሳ ከረጅም ዓመታት በኋላ በድጋሚ ተገናኝተዋል።

አትሌት ፋጡማ ሮባ በታሪካዊው የአትላንታ ኦሎምፒክ በሴቶች ማራቶን ውድድር ለኢትዮጵያ ከአርባ ዓመታት በኋላ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘች ታላቅ ባለውለታ ናት።

በወቅቱ ይህንን ታላቅ ድል ተቀዳጅታ ወደ ሀገሯ ስትመለስ በነበረው ከፍተኛ የደስታ ድባብ ውስጥ ጋዜጠኛ ካሳሁን ፈይሳ ለኢትዮጵያ ሬድዮ ፕሮግራም የሚሆን አጭር ቃለ መጠይቅ አድርጎላት እንደነበር ይታወሳል።

ያኔ በወጣትነት ዘመናቸው በስራ አጋጣሚ ተገናኝተው የተነሱትን የማይረሳ ትዝታ የያዘ ፎቶግራፍ በማስታወስ፣ ከአያሌ ዓመታት በኋላ አሁን ላይ በድጋሚ በመገናኘታቸው ለተባረከው ዕድሜና ለአምላክ ምስጋና በማቅረብ ለታዋቂዋ አትሌት መልካም ጤንነትና ረጅም ዕድሜ ተመኝቷል።

ጋዜጠኛ ካሳሁን ፈይሳ በኦንታሪዮ፣ ቶሮንቶ ካናዳ 🇨🇦 ነዋሪ ነው።

#sport #marathon #atlanta1996 #olympics #athletics #history #legend #ethiopianathletes #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2