የዲያስፖራ የባንክ ሂሳብ እገዳን ለማንሳት የተዘጋጀ አዲስ መመሪያ​የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) …

- Advertisement -
Sidebar AD
የዲያስፖራ የባንክ ሂሳብ እገዳን ለማንሳት የተዘጋጀ አዲስ መመሪያ
​የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ቁጥርን ከባንክ ሂሳብ ጋር ባለማያያዝ ምክንያት የታገዱ የዲያስፖራ ደንበኞችን ሂሳብ በጊዜያዊነት ለመክፈት የሚያስችሉ አማራጭ መንገዶችን ይፋ አደረገ።
ባንኩ ይህንን ያስታወቀው ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ለኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት በጻፈው ይፋዊ ደብዳቤ ነው።
​በመመሪያው መሰረት፣ ሂሳብ በከፈቱበት ወቅት የመኖሪያ አድራሻቸውን ከኢትዮጵያ ውጭ ማድረጋቸውን በባንኩ የመረጃ ቋት ላይ ያስመዘገቡ ደንበኞች ሂሳባቸው አልታገደም።
ሆኖም አድራሻቸውን ያላስመዘገቡና ሂሳባቸው የታገደባቸው ደንበኞች፣ የፋይዳ መታወቂያ ማቅረብ ባይችሉም እንኳ በውጭ ሀገር መኖራቸውን የሚያረጋግጡ ተለዋጭ ማስረጃዎችን በማቅረብ እገዳውን ማንሳት ይችላሉ።
​ደንበኞች እገዳውን ለማንሳት የሚከተሉትን ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፦
👉​የውጭ ሀገር የመኖሪያ ፈቃድ (Residence Permit/ID)፣ የትምህርት ወይም የህክምና ማስረጃ።
👉​በህጋዊ አካል የተረጋገጠ እና በውጭ ሀገር እንደሚኖሩ የሚገልጽ የውክልና ማስረጃ (በወኪሎቻቸው በኩል)።
👉​ለዲፕሎማቶች የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ መታወቂያ።
👉​በውጭ ሀገር በሚገኝ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ጽሕፈት ቤት በኩል በቀጥታ በኢሜል የሚላክ ማረጋገጫ።
​የዲያስፖራ ደንበኞች እነዚህን ማስረጃዎች ሂሳባቸው ለተከፈተበት የባንክ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ ኢሜል ወይም በዋናው መስሪያ ቤት ለሚገኘው የዲያስፖራ ባንኪንግ ክፍል (DiasporaBanking@cbe.com.et) በመላክ እገዳው በጊዜያዊነት እንዲነሳላቸው ማድረግ ይችላሉ።
​በሌላ በኩል፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) ለሚኖሩ የኢትዮጵያ ዜጎች እዚያው ባሉበት ቦታ የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ማካሄድ የሚችሉ በመሆኑ፣ ይህ ጊዜያዊ መመሪያ እንደማይመለከታቸው ባንኩ አስታውቋል።

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: