* የአለም ዋንጫ ጨዋታዎችን በነፃ ያስተላልፋል
#Ethiopia | የሀገሬ ቴሌቪዥን የዓለም ዋንጫን በቀጥታ የማስተላለፍ መብት ማግኘቱን ተከትሎ ከቀድሞው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ኢቢሲ ጋር በተያያዘ እገዳ ሊጣልበት ነው በሚል በማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨው መረጃ ሙሉ በሙሉ ከእውነት የራቀ መሆኑን የጣቢያው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ንዋይ ይመር ገለጹ።
ዋና ስራ አስፈፃሚው ከታዲያስ አዲስ የሬዲዮ ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት የጣቢያው የስርጭት መብት ሙሉ በሙሉ ህጋዊ በሆነ መንገድ የተገኘ መሆኑን አስረድተዋል።
የስምምነቱን ህጋዊነት በተመለከተም ስርጭቱ የተገኘው የፊፋ ወኪል ከሆነው የፈረንሳዩ ኒው ወርልድ ቲቪ ኩባንያ ጋር በስዊዘርላንድ ህግ መሰረት አለምአቀፋዊ ውል በመፈረም በመሆኑ በሀገር ውስጥ የሚወሩ ወሬዎች ስምምነቱን ሊያስተጓጉሉ እንደማይችሉ ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣንን አቋም በተመለከተም ከባለስልጣኑ ኃላፊዎች ጋር መነጋገራቸውንና ምንም አይነት እገዳን የሚጠቁም ደብዳቤም ሆነ ስሜት አለመኖሩን አረጋግጠዋል።
በሌላ በኩል ከቶጎ ሎሜ የመጡ የፊፋ የቴክኒክ ባለሙያዎች ለጣቢያው ሰራተኞች የስርጭትና የቴክኒክ ስልጠናዎችን ሰጥተው ማጠናቀቃቸውንና ጣቢያው ስርጭቱን ለመጀመር በሙሉ ዝግጅት ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
በመጨረሻም ስፖርት አፍቃሪው ማህበረሰብና ስፖንሰር አድራጊ ድርጅቶች በማህበራዊ ሚዲያ በሚለቀቁ ላልተረጋገጡ ወሬዎች ሳይደናገጡ የሀገሬ ቲቪ በኢትዮሳት ሳተላይት አማካኝነት ጨዋታዎቹን በነፃ ወደ እያንዳንዱ ቤት እንደሚያደርስ ዋና ስራ አስፈፃሚው ማረጋገጫ ሰጥተዋል።
#worldcup #hagaretv #sports #football #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Source: GetuTemesgen








No comments yet.