“ስለ አንተ ሁልጊዜም ተገድለናል እንደሚታረዱም በጎች ሆነናል።

- Advertisement -
Sidebar AD

መዝ 43:22

የኀዘን መግለጫ

#Ethiopia | እስመ በእንቲአከ ይቀትሉነ ኩሎ አሚረ። ወኮነ ከመ አባግዕ ዘይጠብሑ
መዝ 43:22

Waa’ee Keetif Yeroo Hunda Duuna, Akka Hoolota qalamaniis Taane. Far 43:22

ከግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ:ም ጀምሮ በአርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ ወረዳ በሺርካ ወረዳና ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ 13 ኦርቶዶክሳውያን ሲገደሉ፤ የ101 ዓመት ዕድሜ ያለው የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ወድሟል።

የካራ ኩፍተና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ላይም ዘረፋ የተካሄደ ሲሆን ምእመናን ጽላቱን ይዘው ተሰደዋል፤ መኖሪያ ቤታቸውም ተቃጥሏል።

የተገደሉ ሰዎች ስም ዝርዝርም

1. አቶ ደምረው አበራ የ70 ዓመት
2. ከፈለኝ ልክየለው የ56ዓመት
3. ሐይሉ ንጉሴ የ70 ዓመት
4. እሸቴ ዳመና የ42 ዓመት
5. አበባየሁ ዳኜ የ42 ዓመት
6. ሰሙ አባይነህ የ70 ዓመት
7. 1 ሚሊሻ
8. አማረ በላይነህ የ80 ዓመት
9. ተሬ ደሴ የ25 ዓመት
10. ወጣት ገነነ ጥላሁን በሽርካ ወረዳ
11. ሙርቴሳ ጥላሁን በሽርካ ወረዳ
12. አቶ ንጉሱ ማንደፍሮ በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ
13. አቶ በቀለ ኃ/ሚካኤል በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ

በአጠቃላይ የ13 ሰዎች ህይወት አልፈዋል።
በተጨማሪ በአሰኮ ወረዳ ከ280 ሰው በላይ ተፈናቅለዋል።
በመሆኑም ኦርቶዶክሳውያኑ ተወልደው ካደጉበት፣ ወልደው ከሳሙበት ቀያቸው በሃይማኖታቸው ብቻ ቤታቸው እየተለየ ተቃጥሏል፤ ንብረታቸውና ከብቶቻቸው ተዘርፈዋል። ከጥቃቱ የተረፉት ነዋሪዎችም ይዘውት የሸሹት እምነታቸውንና ማንነታቸውን ብቻ በመሆኑ አሁን ላይ ሜዳ ላይ ወድቀው ይገኛሉ ።

ስለዚህ በተፈጸመው ጥቃት የተሰማነን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽን የሞቱትን ወገኖቻችን (ልጆቻችን) እግዚአብሔር አምላክ ነፍሳቸውን ይማርልን (በመንግሥተ ሰማያት ያሳርፍልን) የዘኑትን እና የተፈናቀሉትን ወገኖቻችን(ልጆቻችን) እግዚአብሔር ያጽናናልን።

ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ
የአርሲና ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
የቅዱስ ሲኖዶስ አባል


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: