ቢቢሲ በአርሲ በደረሰው ጥቃት ላይ መረጃ ለመጠየቅ ለኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ እና የክልሉ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አራርሳ መርዳሳ በተደጋጋሚ ቢደውልም ስልካቸው ባለመነሳቱ ምላሽ ማግኘት አልቻለም።
ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ የአርሲ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑትን አቶ ሶሪ ወጊን ስለተፈጸመው ጥቃት ማክሰኞ አመሻሽ ላይ ላቀረበላቸው ጥያቄ “እስከአሁን የደረሰን መረጃ የለም፤ እናጣራለን” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ጥቃቱ ከተፈጸመባቸው አካበቢዎች አንዱ የሆነው የሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ አስተዳዳሪ ሐሰን መሐመድም ሰዎች ስለሞቱበት እና ንብረት ስለወደመበት ክስተት “መረጃ የለንም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
Source: FastMereja









No comments yet.