ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከእንጦጦ እስከ ቀጨኔ መድኃኔዓለም ያለው የመልሶ ማልማት እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በይፋ መርቀው ሥራ አስጀመሩ
#Ethiopia | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ማግስት፣ ዛሬ ጠዋት ከእንጦጦ እስከ ቀጨኔ መድኃኔዓለም ያለውን የመልሶ ማልማት እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት መርቀው በይፋ ሥራ ማስጀመራቸውን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት፣ ይህ ትልቅ ተነሣሽነት፤ የተራቆቱ አካባቢዎችን በዘመናዊ የአፈር ጥበቃ እና በወንዝ ማጣራት ወደ አረንጓዴ ስፍራዎች በመቀየር፣ የፍራፍሬ ፓርኮችን ከእግር ጉዞ እና ከብስክሌት መንገዶች ጋር በማቀናጀት መዲናችንን አድሷል ብለዋል።
በአጠቃላይ 22.25 ኪሎ ሜትር የወንዝ ዳርቻ ልማትን የሚሸፍነው ይህ ፕሮጀክት፣ የማይቆራረጥ የልማት ሥራችን ሕያው ምስክር ከመሆኑም በላይ የሀገራዊ ዕድገታችን፣ የአካባቢ ጥበቃ እና የከተማ እድሳት በተግባር የታየበት ነው ሲሉም አክለዋል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu



Source: GetuTemesgen









No comments yet.