ችሎት ውስጥ የተፈፀመ አሰቃቂ ግድያዛሬ ረፋድ ላይ በሆለታ ወልመራ ወረዳ ፍርድ ቤት ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት፣ የዕለቱን የችሎት ው…

- Advertisement -
Sidebar AD
ችሎት ውስጥ የተፈፀመ አሰቃቂ ግድያ
ዛሬ ረፋድ ላይ በሆለታ ወልመራ ወረዳ ፍርድ ቤት ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት፣ የዕለቱን የችሎት ውሳኔ በማንበብ ላይ የነበሩ ዳኛ እና አንዲት ተከራካሪ ህይወታቸው ማለፉን አክሰስ ቱ ጃስቲስ ኢኒሼቲቭ – ኢትዮጵያ አስታውቋል።
እንደ ምንጩ መረጃ፣ የቤተሰብ ክርክር ጉዳይን በመመልከት ላይ የነበሩት ዳኛ ወርቄ ፈካንሳ የፍርድ ውሳኔውን እያነበቡ ባሉበት ወቅት፣ ተከሳሹ በድንገት ባወጣው ሽጉጥ ዳኛዋን በጥይት በመምታት ህይወታቸውን ቀጥፏል።
በዚሁ አጋጣሚ በችሎቱ ላይ በጉዳዩ ላይ ይከራከሩ የነበሩት (ተከራካሪዋ) በተመሳሳይ ሁኔታ በተከሳሹ በተተኮሰ ጥይት ወዲያውኑ ህይወታቸው አልፏል።
የሕግ ባለሙያዎችና ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ድርጊቱን በጽኑ ያኮነኑ ሲሆን፤ ዳኞችና የሕግ ባለሙያዎች በሥራ ገበታቸው ላይ አስተማማኝ የደህንነት ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ በርካቶች በመጻፍ ላይ ይገኛሉ።
“አንድ ግለሰብ ታጥቆ ወደ ፍርድ ቤት አዳራሽ መግባት መቻሉ፣ የፍርድ ቤቶችን የጸጥታና የፍተሻ አሰራር ምን ያህል ደካማ እንደሆነ በአሳዛኝ ሁኔታ አሳይቷል” በማለት አክሰስ ቱ ጃስቲስ ኢኒሼቲቭ የድርጊቱን አሳሳቢነት ገልጿል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: