የዓለም የፕሬስ ነፃነት ታይቶ
በማይታወቅ ሁኔታ አሽቆልቁሏል
የድንበር የለሽ ጋዜጠኞች ድርጅት (RSF) ባወጣው የ25ኛ ዓመት ዓለም አቀፍ መግለጫ መሠረት፣ በዓለም ዙሪያ የሚዲያ ነፃነት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ማሽቆልቆሉንና ጋዜጠኝነትን ወደ ወንጀል የመቀየር ሂደት መባባሱን አስታውቋል።
በአሁኑ ወቅት አምባገነን መንግሥታት የሚዲያ ነፃነትን ለማፈን የብሔራዊ ደኅንነት ሕግጋትን እንደ መሣሪያ እየተጠቀሙበት እንደሚገኙ ድርጅቱ የገለጸ ሲሆን፣ ኖርዌይ ለ10ኛ ተከታታይ ዓመት 1ኛ ደረጃን በመያዝ የዓለም የፕሬስ ነጻነትን በማስፈን ግንባር ቀደምነቷን አስመስክራለች። በአንጻሩ አሜሪካ በሚዲያ ላይ በሚሰነዘሩ የፖለቲካ ጥቃቶች ምክንያት በ7 ደረጃዎች በማሽቆልቆል 64ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
በዚሁ ዓለም አቀፍ የደረጃ ሰንጠረዥ መሠረት ኢትዮጵያ ከ180 የዓለም ሀገራት መካከል 148ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፤ ለዚህም በሀገሪቱ አራት ጋዜጠኞች ከፀረ-ሽብርተኝነት ሕግ ጋር በተያያዘ ክስ ለሦስት ዓመታት ታስረው መቆየታቸው በሕጋዊ መመዘኛ ዝቅተኛ ውጤት እንድታገኝ ማድረጉ ተገልጿል። ከአፍሪካ ቀንድ ሀገራት መካከል የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ የምትገኘው ሱዳን 161ኛ ደረጃን ስትይዝ፣ ኤርትራ ደግሞ 180ኛ በመሆን ከዓለም የመጨረሻውን ደረጃ ይዛለች።
@Seledadotio

No comments yet.