የፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋቾች ማሕበር የዓመቱ ምርጥ እጩዎች ይፋ ሆኑ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋቾች ማሕበር የ2025/26 የውድድር ዓመት የዓመቱ ምርጥ እጩዎች ይፋ ሆነዋል፡፡

በዚህም አርሰናል ሦስት ተጫዋቾችን በእጩነት በማስመረጥ ቀዳሚ ሲሆን÷ ጋብሬል ማጋሌሽ፣ ዴቪድ ራያ እና ዴክላን ራይስ በእጩነት ቀርበዋል፡፡

የመድፈኞቹ ግብ ጠባቂ ዴቪድ ራያ በውድድር ዓመቱ በ19 ጨዋታዎች ግብ ሳይቆጠርበት በመውጣት የወርቅ ጓንቱን ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

ጋብሬል ማጋሌሽ እና ዴክላን ራይስ አርሰናል የሊጉን ዋንጫ እንዲያሳካ ትልቁን አስተዋጽኦ ካበረከቱ ተጫዋቾች መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን ያሸነፈው የማንቼስተር ዩናይትድ የመሐል ሜዳ ተጫዋች ብሩኖ ፈርናንዴዝ ሌላኛው በእጩ ዝርዝር ውስጥ የተካተተ ተጫዋች ነው፡፡

ብሩኖ 21 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻቶ በማቀበል በአንድ የውድድር ዓመት በሊጉ በርካታ ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን የማቀብል ክብረ ወሰኑን የግሉ ማድረጉ አይዘነጋም፡፡

በ27 ግቦች የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን የወርቅ ጫማውን ያሸነፈው ኤርሊንግ ብራውት ሀላንድ እና ረያን ሼርኪ ከማንቼስተር ሲቲ በእጩነት ቀርበዋል፡፡

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
#fmc


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: