ሰርክ አዲስ

- Advertisement -
Sidebar AD

‼️

አዲስ አበባ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ላይ ሆና፦

ሊዮኔል አንድሬስ ሜሲ ስድስተኛ የአለም ዋንጫ ተሳትፎውን አደረገ፥ ለሃገሩ አርጀንቲና 200ኛ ጨዋታውን አከናወነ፤ በአለም ዋንጫ 27ኛ ጨዋታውን ተጫወተ፤ አልጄሪያ ጎል ላይ ሶስት ጊዜ ተመላለሰ፤ አለምን አስደመመ

አርጀንቲና እኩለ ለሊት ላይ ሆና፦

የሃገሯ ልጅ ሜሲ በአለም ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ሃትሪክ ሲሰራ አየች፤ በአለም ዋንጫ ታሪክ በእድሜ ትልቁ ሃትሪክ ሰሪ ሲሆን እማኝ ሆነች፤ በአለም ዋንጫ 16ኛ ጎሉን አግብቶ ከጀርመናዊው ሚሊስሎቭ ክሎዝ ጋር ታሪክ ሲጋራ መዘገበች፤ የአርጀንቲና የምንግዜም ኮከብ ግብ አግቢነትን 120 ጎል ሲያደርስ በደስታ ዘለለች፤ ቦነስ አይረስ በሃሴት ነደደች

ህንድ ኒውደልሂ ማለዳ ላይ ከእንቅልፏ እንደነቃች፥ አውስትራሊያ ሜልቦርን እኩለ ቀን ላይ ለምሳ እንደተዘጋጀች፥ ጨዋታውን ያስተናገደችው የአሜሪካዋ ካንሳስ ምሽት ላይ ለመኝታ እየተሰናዳች፥ አለም በተለያየ የሰአት ልዩነት ውስጥ ሆና የሊዮኔል ሜሲን ጀብዱ በአይኗ ተመለከተች፤ የወቅቱ የአለም ሻምፒዮን ሜሲ ከአልጄሪያ ጋር፦

⚽ ለ80 ደቂቃ ተጫወተ
⚽ 57 ኳስ ነካ
⚽ 30 የተሳካ ኳስ አቀበለ
⚽ 81% የኳስ ማቀበል ስኬት አስመዘገበ
⚽ 6 ሙከራ አሳየ
⚽ 4 ኢላማ የጠበቀ ሙከራ አደረገ
⚽ የዚነዲን ዚዳን ልጅ የአልጄሪያው ግብጠባቂ ሉካ ዚዳን ላይ 3 ጎል አገባ፤ አርጀንቲና 3-0 አሸንፋ ወጣች

ከ20 አመት በፊት ሰኔ 9/1998 በጀርመኑ አለም ዋንጫ በምድብ ሶስት አርጀንቲና ሰርቢያ ሞንቴኔግሮን 6-0 ስታሸንፍ ወጣቱ ሊዮኔል አንድሬስ ሜሲ 75ኛ ደቂቃ ላይ ተቀይሮ ገብቶ 88ኛ ደቂቃ ላይ ጎል አስቆጥሮ ነበር፤ ያኔ በ18 አመት 357 ቀን በአለም ዋንጫ ጎል ያገባ ትንሹ አርጀንቲናዊ ተጫዋች ተባለ

ከ20 አመት በኋላ በተመሳሳይ ቀን፥ በተለየ አመት ትናንት ሰኔ 9/2018 ደግሞ በአለም ዋንጫ ምድብ 10 አርጀንቲና አልጄሪያን 3-0 ስታሸንፍ ጎልማሳው ሊዮኔል አንድሬስ ሜሲ ሃገሩን በአንበልነት እየመራ ሃትሪክ ሰራ፤ በ38 አመት 357 ቀን በአለም ዋንጫ ጎል ያገባ አንጋፋው አርጀንቲናዊ ተጫዋች ሆነ፤ እድሜ ያልገደበው ሰርክ አዲሱ ሜሲ!

በጋዜጠኛ ታምሩ ዓለሙ


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: