አዲስ የመንገድ ደህንነት መመሪያ
በትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ተሽከርካሪዎች፣ ሁሉም ተሳፋሪዎቻቸው ደረጃውን የጠበቀ የደህንነት ቀበቶ (Seat Belt) እንዲያስሩ የሚያስገድድ አዲስ መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑ ተገለጸ
በሃገር አቀፍ ደረጃ የመንገድ ደህንነትን በማስጠበቅ የትራፊክ አደጋዎችን ለመቀነስ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገድ ደህንነትና መድኅን ፈንድ አገልግሎት ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።
በተለይም በአሽከርካሪዎች ላይ የደህንነት ቀበቶ እንዲኖር በማስቻል አደጋዎችን ለመቀነስ ሲሰራ መቆየቱን ያስታወሱት በአገልግሎቱ የመንገድ ደህንነት ህግ ትግበራ ዴስክ ሃላፊ ወ/ሮ ብርክት ባህሩ፤ ሁሉም አሽከርካሪዎች የደህንነት ቀበቶን በተሽከርካሪያቸው ላይ እንዲያስገጥሙ በህግ አስገዳጅ መደረጉንና ህጉን ባልተገበሩት ላይም ህጋዊ እርምጃ ሲወሰድ መቆየቱን አብራርተዋል፡፡
ነገር ግን በአሁኑ ወቅት በርካታ ተሽከርካሪዎች የደህንነት ቀበቶ ቢኖራቸውም፣ ቀበቶዎቹ በትክክል ከአደጋ የማይከላከሉና ደረጃቸውን ያልጠበቁ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ይህንን ችግር ለማስቀረት አዲስ መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በተለይም የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች ከፊት መቀመጫ አንስቶ እስከ ኋላ ወንበር ለሚቀመጡ ተሳፋሪዎች በሙሉ የደህንነት ቀበቶ እንዲገጥሙ የሚያስገድድ አዲስ መመርያ እየተዘጋጀ መሆኑን ገልጸው፤ የሚገጠመው የደህንነት ቀበቶም ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን መስፈርት መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።
መመሪያው አሁን ላይ ወደ ፍትህ ሚኒስቴር መላኩንና ሲጸድቅ በቀጥታ ወደ ስራ እንደሚገባ ገልጸዉ፤ ከደህንነት ቀበቶ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ በተለያዩ አማራጮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም አመላክተዋል ።
መመሪያው ጸድቆ ስራ ሲጀምር፣ ከውጪ የሚገቡም ሆነ በሃገር ውስጥ የሚገጣጠሙ አዳዲስ ተሽከርካሪዎች ደረጃውን እንዲያሟሉ አስገዳጅ እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡ ነባር (የቆዩ) ተሽከርካሪዎችም በጊዜ ሂደት ደረጃውን የጠበቀ ቀበቶ እንዲያሟሉ ይደረጋል ብለዋል።
@Seledadotio

- Advertisement -

No comments yet.