በ2017 በጀት ዓመት 72 የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከግዢ ህግ ውጪ የ1.2 ቢሊዮን ብር ግዢ መፈፀማቸው በኦዲት ተረጋገጠ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የገንዘብ መጠኑ ከ2016 በጀት ዓመት ጋር ሲመሳከር የ800 ሚሊዮን ብር ጭማሪ አለው፡፡

የፌዴራል መንግሥት ባወጣው የግዥ አዋጅ መሰረት ምን ያክል መስሪያ ቤቶች በጨረታ መግዛት ለሚገባቸው ግዥዎች ጨረታ አውጥተዋል እና የዋጋ ማወዳደሪያ ሰብሰበዋል የሚለውን ለማረጋገጥ በተሰራ #ኦዲት 72 መስሪያ ቤቶች ከህግ ውጭ ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ ግዢ መፈጸማቸውን ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት አረጋግጧል፡፡

በዚህም በ29 መሥሪያ ቤቶች በጨረታ መፈጸም ሲገባቸው ያለ ጨረታ በቀጥታ የ441,033,011 ብር ግዢ መፈጸማቸው ተረጋግጧል፡፡

አንድ መሥሪያ ቤት ደግሞ በግልጽ ጨረታ መፈጸም ሲገባው መስፈርቱን ሳያሟላ በውስን ጨረታ የ134,295,220 ብር ጨረታ መፈፀሙን ዋና ኦዲተር ተናግሯል፡፡

እንዲሁም በ22 መሥሪያ ቤቶች ጨረታ ሳይወጣ በዋጋ ማወዳደሪያ 68,534,060 ግዢ የተፈጸመ ሲሆን በ17 መስሪያ ቤቶች ደግሞ በዋጋ ማወዳደሪያ ግዢ መፈጸም ሲገባቸው 409,691,138 ግዢ ፈፅመዋል፡፡

በተጨማሪም 3 መሥሪያ ቤቶች ያለ መስፈርት የ11,170,882 ብር ለቀማ ግዢ ፈጽመዋል፡፡

በተጨማሪም 20 መስሪያ ቤቶች ያለ ኤሌክትሮኒክስ የ194,793,839 ብር ግዢ ፈፅመዋል ይላል ዋና ኦዲተር፡፡

በዚህም በጠቅላላው በብር ከ1 ቢሊዮን 259 ሚሊዮን ብር በላይ ከህግ ውጭ ግዢ የተፈፀመ ሲሆን ይህም ከ2016 ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ800 ሚሊዮን ብር ጭማሪ አለው፡፡

በ2016 በጀት ዓመት ተቋማት ከህግ ውጪ የፈፀሙት የግዢ መጠን 404 ሚሊዮን ነበር፡፡

ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት እነዚህ ተቀሟት ከህግ ውጭ ግዢ እንደፈፀሙ ማሳሰቡን በሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡

credit : ሸገር ኤፍ ኤም

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: