ደቡብ አፍሪካውያን ከአየርላንድ ተባረሩ
#Ethiopia | አየርላንድ በሀገሯ ውስጥ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲኖሩ የነበሩ 42 የደቡብ አፍሪካ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ያባረረች ሲሆን ለዚህም የመንቀሳቀሻ መነሻ ወጪ 735,000 ዩሮ 853,000 ዶላር ማውጣቷን አስታውቃለች።
ይህ የስደት እርምጃ የተወሰደው ግለሰቦቹ በፈቃደኝነት ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የተሰጣቸውን ዕድል ሳይጠቀሙ በመቅረታቸው በተላለፈ የማባረር ትዕዛዝ ሲሆን ከተባረሩት መካከል ሁለቱ የወንጀል ሪከርድ ያለባቸው መሆኑ ታውቋል።
ይህ ከአየርላንድ የተሰማው ዜና በአሁኑ ወቅት በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ስለ ስደት ስለ መጤ ወንድምን ማሳደደ እና ሰነድ የሌላቸው የውጭ ዜጎች ማዋከብ ላይ የሚደረገውን የጦፈ ክርክር እና ውጥረት ዳግም ቀስቅሶታል።
የዚህ የስደት እርምጃ መጨመር እንደሚያሳየው፣ የስደት ጉዳይ ለደቡብ አፍሪካ “ባለ ሁለት ገፅታ” ፈተና እየሆነባት መጥቷል። በአንድ በኩል በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ዜጎቿ በሕገ-ወጥ ስደት ምክንያት እየተባረሩ የሚመለሱባት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በሀገሯ ውስጥ ከሚኖሩ የውጭ ዜጎች ጋር በተያያዘ ከሕዝብ የሚነሳባትን ጠንካራ ተቃውሞ እና የስደተኞች ጥላቻ ስጋትን ለማስተናገድ እየተገደደች ትገኛለች።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.