Ethiopian B Boy B Girl dancer (የኢትዩ ቢ ቦይና ቢ ገርል) ብሬክ ዳንስ ውድድር በአድዋ ድል መታሰቢያ ፊት ለ

- Advertisement -
Sidebar AD

Ethiopian B Boy B Girl dancer (የኢትዩ ቢ ቦይና ቢ ገርል) ብሬክ ዳንስ ውድድር በአድዋ ድል መታሰቢያ ፊት ለፊት በድምቀት ተካሄደ ።

ባሳለፈንው ቅዳሜ ሰኔ 13/2018 ዓ.ም ለስድስት ወር ‘Building unity and inclusive opportunities through sport and dialogue’ በሚል ስያሜ እየተተገበረ ባለ ፕሮጀክት ስር የታቀፉ አርባ አምስት የሚደርሱ ታዳጊ ወጣቶች ተከታታይ የዳንስ እና የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ሲወስዱ ቆይተው ከፕሮጀክቱ መጠናቀቅ አስቀድመው ይህን የግል የዳንስ ውድድር አቅርበዋል።
ይህ ፕሮጀክት Nutrition for education and development (N4ED) ከፈረንሳይ ኤምባሲ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ከሀዊ ዳንስ ኢንተርቴይመንት እና እሺ ሚዲያ ጋር በትብብር እየተተገበረ ያለ ፕሮጀክት ሲሆን ወጣት ሴቶች እና ወንዶችን እዲሁም ከአካል ጉዳት ጋር ያሉ ወጣቶችን በአንድ ላይ በማቀፍ ባለተሰጥዎ እና ድንቅ ብቃት ያላቸው ወጣቶችን እያፈራ ይገኛል።
በዕለቱ የከተማችን B Boy እና B Girl ልምድ ባላቸው ዳኞች የተመረጡ ሲሆን የተለያዩ ማበረታቻዎችም በፕሮጀክቱ ማጠቃለያ ላይ ይበረከትላቸዋል።
የመዝጊያ ፕሮግራም እና የብሬክ ዳንሰኞች የምርቃት ዝግጅት አርብ ሰኔ 19/2018 በአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴስ ጥሪ በተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይካሄዳል ።

በዚህ አጋጣሚ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሀላፊዎች ለዚህ ደማቅ የጎዳና ላይ ትርኢትና ዝግጅት ላበረከቱት አስተዋፅኦ አዘጋጆቹ ከልብ እናመሰግናለን ።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: