‎በኪነጥበብ የታጀበ ደግነት

- Advertisement -
Sidebar AD

🙏

‎ኮሜዲያን አስረስ በቀለ (ቼሪ) የመጽሐፉን ገቢ ሙሉ ለሙሉ ለበጎ አድራጎት አበረከተ

‎​የሕፃናት መጻሕፍት ደራሲና የልጆች ፕሮግራም አዘጋጅ በመሆን፣ በተለይም “ቼሪ” የተሰኘውን ተወዳጅ የልጆች ካራክተር (ገጸ-ባህሪ) በመፍጠር በሕፃናት መዝናኛና ትምህርት ዘርፍ ጉልህ አሻራ ያሳረፈው ታዋቂው ኮሜዲያን አስረስ በቀለ፣ በድጋሚ የደግነት ተምሳሌትነቱን አሳይቷል።

‎ሰሞኑን በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) ካስመረቃቸው ሁለት አዳዲስ የሕፃናት መጻሕፍት መካከል የመጀመሪያውን መጽሐፍ ሽያጭ ገቢ ሙሉ ለሙሉ ለሙዳይ በጎ አድራጎት ድርጅት በስጦታ አበርክቷል።

‎​ከ15 በላይ የልጆች ተረት መጻሕፍትን ለንባብ ያበቃው ደራሲ አስረስ በቀለ፣ ለሕፃናት ሥነ-ጽሑፍ ባበረከተው ከፍተኛ አስተዋፅኦ እ.ኤ.አ በ2022 በተካሄደው Ethiopia Reads Children’s Reading Summit ላይ እውቅና የተቸረው አንጋፋ ባለሙያ ነው።

‎ ይህ የሰሞኑን ስጦታውም ጥበብን ከሕዝብ ወገንተኝነት ጋር አጣምሮ የመጓዙ ማረጋገጫ ሆኗል።

‎​ይህንን ታላቅ የበጎ አድራጎት ስጦታ የተቀበለው የሙዳይ በጎ አድራጎት ድርጅት፣ ለረጅም ዓመታት በችግር ውስጥ ያሉ ሕፃናትን፣ እናቶችንና አረጋውያንን በመደገፍና ተስፋ በመሆን የሚታወቅ ተቋም ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በአቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 2 አድራሻውን አድርጎ ሰብአዊ አገልግሎቱን በስፋት እየሰጠ ይገኛል።

‎​የድርጅቱ መሥራች ወይዘሮ ሙዳይ ምትኩ የተደረገላቸውን ድጋፍ አስመልክተው ባስተላለፉት ልባዊ መልእክት፦

‎​”አስረስ በቀለ (ቼሪ) የምንግዜም የልብ አጋራችንና ታማኝ ደጋፊያችን ነው። ዛሬም ይህንን የመጽሐፉን ገቢ ሙሉ ለሙሉ ለእኛ በማበርከት ያደረገልንን ታላቅ በጎ ተግባር ስንመለከት ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን።”

‎​በማለት አክለውም ለመላው የሀገራችንን ሕዝብ ጥሪ አቅርበዋል፦
‎​”ሁሌም ከጎናችን የማትለዩ ደጋግ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፤ ይህንን ጠቃሚ የሕፃናት መጽሐፍ በመግዛት፣ በአንድ በኩል የልጆቻችሁን የዕውቀት አድማስ እንድታሰፉ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የሽያጩን ገቢ በቀጥታ ለሙዳይ በማዋል አቅመ-ደካሞችንና ሕፃናትን እንድትደግፉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።”

‎​ይህንን መጽሐፍ በመግዛት የዕውቀትና የቸርነት አጋር እንሁን!





Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1