አርቲስት ካሙዙ ካሳ በየካ ክፍለ ከተማ በከፍተኛ ድምፅ ማሸነፉን አስታወቀ
በየካ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲን ወክሎ ለምርጫ የቀረበው ታዋቂው አርቲስት ካሙዙ ካሳ፣ ከአካባቢው ነዋሪዎች ከፍተኛ ድምፅ በማግኘት ማሸነፉን በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። አርቲስቱ የምርጫውን ውጤት ተከትሎ ለነዋሪዎችና ለመራጮች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፈ ሲሆን፣ ለተደረገለት ድጋፍም ጥልቅ ምስጋናውን አቅርቧል።
“እንደ ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ ድምፅ ማግኘታችንና በአካባቢው ማሸነፋችን ታላቅ ድል ነው” ሲል የገለጸው አርቲስት ካሙዙ፣ ይህ ውጤት የህዝብ ድል መሆኑን በመጥቀስ፣ “ኢትዮጵያ አሸንፋለች” የሚል መልዕክት በድል አድራጊነት ስሜት አስተላልፏል።
@Seledadotio

- Advertisement -

No comments yet.